Print this page
Saturday, 11 August 2018 10:22

የአዲስ አበባ አስተዳደር አዳዲስ የካቢኔ አባላትን ሾመ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

-    “የተሿሚዎች መስፈርት ብቃት፣ ልምድና ኢትዮጵያዊነት ነው”
 
ቀደም ሲል 33 የካቢኔ አባላት የነበሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ የካቢኔ አባላቱን ወደ 18 ዝቅያደረገ ሲሆን አዳዲስ የካቢኔው አባላትም በም/ከንቲባው አቅራቢነት በምክር ቤቱ ተሾመዋል፡፡
አስራ ስምንቱ የካቢኔ አባላትም የከተማ አስተዳደሩ ም/ቤት አፈጉባኤ የነበሩት ዶ/ር ታቦር ገ/መድህን የትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣ ረ/ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ፣ ኢ/ር ሰናይት ዳምጠው
የቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የጥቃቅን እና አነስተኛ ቢሮ ኃላፊ፣ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ የጤና ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ደረጀ ፈቃዱ የፕላን ኮሚሽን ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡
በተጨማሪም ኢ/ር ሽመልስ እሸቱ የመሬት ልማትና ማናጅመንት ቢሮ ሃላፊ፣ ኢ/ር ዮናስ አያሌው የኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ዘውዴ ቀፀላ የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ሺሰማ
ገ/ስላሴ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ሮኤ ኖፎላ የፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ወ/ሮ ፍሬህይወት ተፈራ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ጀማል ጀምበር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አብዱልፈታ ዮሱፍ
የንግድ ቢሮ ኃላፊ፣ ወ/ሮ አልማዝ አብረሃ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፣ ወ/ሮ ፍሬህይወት ገ/ህይወት የፐብሊክ ሰርቪስ ሠው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ኢ/ር ኤርሚያስ ኪሮስ የኢንዱስትሪ ቢሮ
ኃላፊ እንዲሁም አቶ አሠፋ ዮሐንስ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊዎች ሆነው መሾማቸው ታውቋል፡፡ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ በመሆን ተመርጠዋል፡፡ ተሿሚዎች የተመረጡበት መስፈርት ብቃት ልምድና ኢትዮጵያዊነት መሆኑን ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡

Read 2999 times