Saturday, 12 May 2012 09:15

“ተወራራሽ ሕልሞች” እና “የኢትዮጵያ የግብር ሕግ” ለንባብ በቁ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

በሰለሞን ሽፈራው የተዘጋጁ 102 በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ሲወጡ የነበሩና ሌሎች ግጥሞች የተካተቱበት “ተወራራሽ ሕልሞች” ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ 103 ገፆች ያሉት መጽሐፍ በ20 ብር ይሸጣል፡፡ በመጽሐፉ ጀርባ የሥነጽሑፍ ምሁሩ የኮተቤው የሻው ተሰማ “ይህን ግጥም መዝሙሬ ባደርገው ደስ ይለኛል” ብሏል፡፡ መጽሐፉ ዛሬ ከጧቱ 3 ሰዓት በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት ይመረቃል፡፡ በሌላም በኩል “የኢትዮጵያ የግብር “Tax” ሕግ፣ ደንቦች፣ ባህርያት፣ መርሆችና ሥርአት ማብራርያ“ መጽሐፍ ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ በዶ/ር ግርማ ግዛው የተዘጋጀው ባለ 164 ገጽ መጽሐፍ ዋጋ 45 ብር ነው፡፡

 

 

Read 2060 times Last modified on Saturday, 12 May 2012 09:17