Saturday, 11 August 2018 10:47

“ከትግል ትዝታዎቼ” መፅሐፍ እየተነበበ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በአንጋፋው የህወሓት ታጋይና መስራች ግደይ ዘርአጽዮን የተፃፈው “ከግል ትዝታዎቼ” የተሰኘ መፅሐፍ ገበያ ላይ ውሏል፡፡ ታጋዩ ጸሃፊ፤ በሴረኞች ተቀጨ የሚሉትን የደደቢት አብዮት በስፋት በሚተረኩበት በዚህ መጽሐፋቸው፤ህወሓትን አስመልክቶ በጭፍን ጥላቻ ስለተፃፉ መፅሐፍትና በህወሓት ውስጥ ያልሰሩትን ሰሩ ብሎ ግለሰቦችን በማሞገስ ህዝቡ የአምልኮ ያህል እንዲቀበላቸው የተደረገበትን መንገድ ያጋልጣሉ፡፡ ስለ ድርጅቱ በመጠኑም ቢሆን በሚዛናዊነት የጻፉ ግለሰቦችን የሚጠቅሱት የህወኃት መሥራች፤ሁሉም ፀሐፍት ለአሁኑ መፅሐፋቸው መነሻ በመሆናቸው አመስግነዋል፡፡
ከድርጅቱ እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስ በከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ እንደነበሩ በመግለፅም፤ ትክክለኛውን የህወሓትን መልክና ቁመና በትክክለኛው መንገድ ለማሳየት ጥረት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡ የተለያዩ ሰነዶችንና ምስሎችን ጨምሮ በ261 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ200 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ክብሩ መፅሐፍት መደብር እያከፋፈለው መሆኑ ታውቋል፡፡

Read 4990 times