Monday, 13 August 2018 00:00

የዳንኤል ክብረት “የአዲስ አበባ ውሾች” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(12 votes)

 “-- አሪፍ ውሻ ማለት ክፉ ውሻ ነው፣ እንደ ማለት ነው፡፡ አንተ ክፉ ውሻ ከሆንክ ለጌቶችህ አሪፍ ውሻ ነህ፡፡ ትናከስላቸዋለህ፣ ትጮህላቸዋለህ፣ መንገድ አላፊውን ታስደነብርላቸዋለህ፣ ታስፈራራላቸዋለህ። ለሌላው ክፉ ስትሆን ለጌቶችህ ምርጥ ውሻ ትሆናለህ። በኋላ ላይ ግን እዳው አንተ ላይ ይወድቃል፤ በመጨረሻ አንተው ትወረወራለህ፤ ለጅቦቹም ተላልፈህ ትሰጣለህ-”
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከላይ እንዳነበባችሁት ስለ “የአዲስ አበባ ውሾች” ያወጋናል- በአዲሱ መፅሐፉ። የአዲስ አበባ ውሾች ግን ተምሳሌታዊ ናቸው - ደራሲው የቀረፃቸው ሰውን እንዲወክሉለት ነው፡፡ ታሪኩ የፖለቲካና ማህበራዊ ስላቅ ሊባል ይችላል። ስለ ዘመኑ ሙሰኛ የመንግስት ባለሥልጣናት፣ ስለ ሞሳኝ ባለፀጎች፣ ስለ ዳያስፖራ ወዘተ … ከጭቁኑ የአዲሳቤ ነዋሪ ጋር እየተነፃፀረ ይተረክልናል - በማራኪ ቋንቋና በሚያዝናና አቀራረብ፡፡
በ253 ገፆች የተቀነበበው የዳንኤል ክብረት መፅሐፍ፤ በ100 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 8334 times