Saturday, 11 August 2018 11:05

የሶማሌ ክልል በልዩ ኮማንድ ፖስት እንዲጠበቅ ተወሰነ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(12 votes)

 በግጭት ውስጥ የሰነበተው የሶማሌ ክልል፣ የፀጥታ ጉዳይ፣ ከፌደራል የፀጥታ አካላትና ከክልሉ ልዩ ኃይል በተውጣጣ ልዩ ኮማንድ ፖስት እንዲጠበቅ ተወሰነ፡፡
ከፌደራል ፖሊስ፣ ከመከላከያ ሰራዊትና ከክልሉ ልዩ ፖሊስ የተውጣጣውና ትናንት ከሰዓት ስራውን በይፋ የጀመረው ኮማንድ ፖስት፤ በደቡብ ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል በላይ ስዩም ይመራል ተብሏል፡፡
ትናንት የፀጥታ አካላቱ የጋራ ስብሰባ አድርገው ኮማንድ ፖስቱ የተመሰረተ ሲሆን በውይይቱም በፀጥታ ጉዳይ በጋራ ተቀናጅተው ለመስራት ተስማምተዋል፡፡ ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች በመከላከያ ሰራዊት ዕዝ ስር ሆነው፣ ለኮማንድ ፖስቱ ተገዥ እንደሚሆኑም ታውቋል፡፡

Read 8780 times