የድምፃዊ ጃሉድ አወል “ንጉሥ” የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን ረቡዕ ለአድማጭ እንደሚቀርብ የአልበሙ ፕሮዲዩሰር አይንአዲስ ተስፋዬ (ዲጄ ፒቹ) አስታወቀ፡፡ ተሰርቶ ለመጠናቀቅ ሁለት ዓመታትን የፈጀውና 1.6 ሚ. ብር እንደወጣበት የተነገረው አልበሙ፤ 17 ዘፈኖችን እንዳካተተና ቅንብሩም በካሙዙ ካሳ (ሻኩራ ስቱዲዮ) እንደተሰራ ተገልጿል፡፡
በድምፅ ቀረፃና ሚክሲንግ ይትባረክ ክፍሉና በማስተሪንጉ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ተሳትፈውበታል ተብሏል፡፡ የድምፃዊው ሁለተኛ የሆነው አልበሙ በአገር ፍቅርና በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ዘፈኖችን እንደተካተቱበት ፕሮዲዩሰሩ አይንአዲ ተስፋዬ (ዲጄ ፒቹ) ተናግሯል፡፡
Saturday, 18 August 2018 09:26
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና