Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 May 2012 09:25

ህፃናት ለእግዚአብሔር የፃፉት ደብዳቤ

Written by 
Rate this item
(7 votes)

ውድ እግዚአብሔር

እባክህ ቆንጆ አድርገኝ፡፡ ምክንያቱም ብልህ ነኝ ብዬ አላስብም፡፡

ቻርሊን

ውድ እግዚአብሔር

የተለያዩ ሃይማኖቶች መፍጠርህ ችግር የለውም፡፡ ግን አንዳንዴ አይደበላለቅብህም?

አሊስን

ውድ እግዚአብሔር

ቄስ ኮሊን ጓደኛህ ናቸው ወይስ በሥራ ጉዳይ ብቻ ነው የምታውቀው?

አኒታ

ውድ እግዚአብሔር

ክረምቱን ብጠብቀውም እስካሁን ተመልሶ አልመጣም፡፡ ብቻ እንዳትረሳው

ማርክ

ውድ እግዚአብሔር

ወንድሜ አይጥ ነው…አይጥ ልትሰጠው ይገባሃል…ሃሃ…ሃ

ዴቪድ

ውድ እግዚአብሔር

ትላንትና የሰራኸውን ቀስተደመና እስክመለከት ድረስ ብርቱካን ቀለም ከወይንጠጅ ጋር የሚስማማ አይመስለኝም ነበር፡፡ አሪፍ ነበር!

ሊዝ

ውድ እግዚአብሔር

ሰንበት ት/ቤት አንተ ሁሉም ቦታ እንዳለህ አስተምረውናል፡፡ ምን ያህል ትልቅ ነህ?

ጄሲ

 

 

 

Read 5598 times Last modified on Saturday, 12 May 2012 09:42