Saturday, 25 August 2018 12:58

“የኔ ትውልድ (My Generation)” ኮንሰርት ዛሬ ይቀርባል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተወዳጅነትን እያገኘ የመጣው ድምፃዊና ዲጄ ሮፍናን “የኔ ትውልድ(My Generation)” የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት ዛሬ ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ ቦሌ በሚገኘው ቃና አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
ሀሴት አኩስቲክ ባንድ ከሁለት ሰዓት ጀምሮ ታዳሚውን እያዝናና ከቆየ በኋላ ዲጄ ሮፍናን ለ90 ደቂቃ ያህል መድረክ ላይ እንደሚያቀነቅን የኮንሰርቱ አዘጋጅ የብሉ ሚዲያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ እስክንድር ፋሲል ተናግረዋል፡፡ ከ2 ሺህ እስከ 2 ሺህ 500 ሰው እንደሚገኝበት የተነገረለት “የኔ ትውልድ ኮንሰርት” ላይ ለመታደም ከዕለቱ ቀደም ብሎ ትኬት ለሚገዛ 250፣ ብር በዕለቱ በር ላይ ለሚገዛ 350 ብር ተተምኖለታል፡፡ ኮንሰርቱ እስከ ምሽቱ 5፡00 እንደሚዘልቅም ለማወቅ ተችሏል፡፡


Read 2075 times