Saturday, 25 August 2018 13:00

“ሲመት” ፊልም ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲና ዳይሬክተር ህልዳና በላይነህ ተፅፎ በሰቨን ኤ ፊልም ፕሮዳክሽን የተዘጋጀው “ሲመት” ፊልም ዛሬ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡
ተሰርቶ ለመጠናቀቅ አምስት ዓመታትን የፈጀውና የ115 ደቂቃ ርዝመት ያለው ፊልሙ፤ በዘመነ መሳፍን የአገዛዝ ሥርዓት ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን የጎንደር ነገስታት ልጆች ከአባታቸው ንግሥናን ለመውረስ የሚያደርጉትን ሽኩቻ ያሳያል ተብሏል፡፡ የማጀቢያ ሙዚቃው በሱልጣን ኑሪ (ሶፊ) የተሰራለት ሲሆን በፊልሙ ላይ አርቲስት ያሬድ ይልማ፣ ይድነቃቸው ተስፋዬ፣ መስከረም አበራ፣ ማስረሻ ፅጌ፣ አንተነህ አስረስ፣ መርዕድ ተስፋዬ፣ ፍቃደሥላሴ ዮሴፍ፣ ፍቅሩ ከበደ፣ ሣራ ተክሌና ሌሎችም አንጋፋና ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል፡፡

Read 2400 times