Saturday, 25 August 2018 13:22

በረከት በትንሳዔ መጣ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(40 votes)

 አዲሱ መፅሐፋቸው ምን ይላል?

   ‹‹የመልካም ዕድል መስኮቶችን የሚያጠቡትን የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ሙስና፣ በትንሽ ድል የመኩራራት እና ለችግሮች ደንታ ቢስ የመሆን፣ እንዲሁም በብሔርተኝነት ጭምብል ያለአንዳች ተጠያቂነት ያሻህን የመስራት አዝማሚያዎችን በጥብቅ ማስወገድ ይጠይቃል››
‹‹በየመድረኩ እንደ ተቀናቃኝ  ሳይሆን እንደ ሐሳብ ቋት (Resource Person) እንድታይ ያቀረብኩት ተማጽኖ በተደፈኑ ጆሮዎች ላይ መውደቁን እያረጋገጥኩ መጣሁ፡፡ ውስጣችንን በውል ለማያውቁ የውጭ ታዛቢዎች ስርዓቱን ከኋላ ሆነን የምናሽከረክረው እኛ ተደርገን የምንታይ ቢሆንም፤ ተመካክሮ መስራት በሌለበትና መገለል በበዛበት ሁኔታ ስያሜው ተሰጠን።››
ጦርነቱ የእርስ በእርስ ጦርነት መሆኑ እስኪጠፋብን ድረስ መሄድ የለብንም። የአንድ ቤተሰብ ልጆች በተለያየ ጎራ ተሰልፈው የሞቱባቸው እናቶች መኖራቸውን እስክንረሳ ድረስ መጓዝ አይገባንም፡፡ አሁን የእነዚህን እናቶች መከራ ለመመልከት ጊዜ መስጠት ይኖርብናል፡፡


Read 12850 times