Saturday, 01 September 2018 15:12

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥራ አሥኪያጅ እና ምክትላቸው ከኃላፊነት ተነሱ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

 የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስራ አስኪያጅ እና ምክትላቸው ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡
በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስራ አስኪያጅነት ከ8 ዓመት በላይ ያገለገሉት አቶ ሰብስቤ ከበደ እና ምክትላቸው አቶ መብርሃቶም ኪሮስ ከኃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያት በግልፅ አለመታወቁን የጠቆሙት የድርጅቱ ሰራተኞች፤ በስራ አስኪያጁ ላይ ከሰራተኞች ሰፊ ቅሬታ ሲቀርብባቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡
የ “አዲስ ዘመን”፣ የ “በሪሳ”፣ የ “ኢትዮጵያን ሄራልድ” እና የ“አል አለም” ጋዜጦችን እና “ዘመን” መፅሔት አሳታሚ የሆነው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ከጋዜጠኝነት ሙያ ይልቅ የገዥው ፓርቲ ፖለቲካዊ አመለካከት የነገሰበት እንዲሆን አድርገዋል በሚል ስራ አስኪያጁ ይወቀሱ እንደነበር ሰራተኞቹ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡
በምትካቸው ዶ/ር ጌትነት ታደሰ በዋና ሥራ አሥኪያጅነት እንዲሁም አቶ ሄኖክ ስዮም እና አቶ ወንድሙ ተክሌ በምክትል ሥራ አሥኪያጅነት እንደተሾሙ ማወቅ ተችሏል፡፡

Read 12562 times