Saturday, 01 September 2018 15:32

“ክብ ልፋት” የግጥም መፅሐፍ ማክሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የገጣሚ መስፍን ወልደተንሳይ “ክብ ልፋት” የተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሀፍ፣ የፊታችን  ማክሰኞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡ ገጣሚው ከዚህ ቀደም በግጥም ምሽቶች በሚያቀርባቸው ግጥሞችና በዘፈን ግጥሞቹ ይታወቃል፡፡
የተለያዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ የተገለፀ ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል መምህራንና ተማሪዎች የሚቀርብ ሙዚቃዊ ተውኔት፣ ግጥሞች በተዋናይ ሚካኤል ሚሊዮንና በ“የማለዳ ኮከቦች” የሚቀርብ ተውኔትና በገጣሚው የተሰራ የሚካኤል በላይነህ አዲስ ዘፈን በድምፃዊው እንደሚቀነቀን ተገልጿል፡፡ መፅሐፉ በ60 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል፡፡ ገጣሚው “በማር ሰራሽ ወይ”፣ “አፋጀሽኝ”፣ “አፍቅሬሻለሁ”፣ “ልወዳት ነው መሰል” እና “ፍቅር አልሸሽም” የተሰኙት የሚካኤል በላይነህ ተወዳጅ ዘፈኖች ግጥም ደራሲ መሆኑ ይታወቃል፡፡  

Read 5065 times