Saturday, 08 September 2018 13:51

ለስኬታማ ትዳር…..ሁለት ቁልፎች

Written by 
Rate this item
(12 votes)

 ትዳር ሲመሰረት በጉጉት የተጠበቀ የግብዣ ወይንም የሙዚቃ በአጠቃላይም የደስታ ስነስርአት ተካሂዶ ነው። አንድን ትዳር ወደትክክለኛው መስመር ለመምራት በዙሪያው ያሉ ዘመድ አዝማዶች በእጅጉ የሚደክሙበት በመሆኑ በኢትዮጵያ አንድ አባባል አለ፡፡እሱም ‹‹…አንዱ ሊያገባ ሌላው ገገባ…›› የሚል ነው፡፡ ይህም በሰርጉ ዙሪያ ያሉ ሰዎች ምን ያህል እንደሚደክሙ የሚያሳይ ነው፡፡ የተጋቢዎች ሁኔታ ደግሞ በወዲፊት ሕይወታቸው ላይ ጥሩ ተስፋ ሰንቀው…ልጅ ሊወልዱ… ሀብት ሊያፈሩ እና ከሞት በስተቀር ምንም ላይለያቸው ለየራሳቸው ቃል ገብተው እንዲሁም መች ነው አብረን የምንውለው የምናድረው ብለው በምኞት እራሳቸውን አዘጋጅተው የሚመሰርቱት ኑሮ ነው፡፡ ነገር ግን ለደስተኛ ትዳር መንገዱ እንደዚህ እንደሚመኙት ቀላል አይደለም፡፡ እንደ Kevin Miller  የስነ ልቡና ባለሙያ እማኝነት፡፡ ስለሆነም ምናልባት በትዳር ግንኙነት ላይ ሳንካ ሲፈጠር ሰዎች የሚያማርሩዋቸው ነገሮች ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ የትዳርን ግንኙነት በጎ ለማድረግ የሚያስችል የሚነበብ መጽሐፍ ወይንም ጋዜጦች አለዚያም እንደሴሚናር ያሉ ስብሰባዎች፤ውይይቶች …ወዘተ የመሳሰሉ ነገሮችን መፈለግ ወይንም መጠበቅ አይቻልም፡፡ ነገር ግን ጥሩ ጊዜ ሲኖር ይቅርታ ማድረግ እና በሰከነ መንገድ መግባባት መቻል ደስተኛ ትዳርን ለመመስረት እጅግ ተፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መካከል መሆናቸውን መርሳት አይገባም፡፡ እነዚህንና የመሳሰሉትን ነገሮች መተግበር ካልተቻለ በትዳር ላይ ጥልቅ የሆነ ችግር ሊከሰት እንደሚችልና ይህንን ችግር ሁለቱ ሰዎች ማለትም ተጋቢዎች መፍታት ካልቻሉ በምንም አይነት መንገድ ሶስተኛ ኃይል ወይንም ሌሎች ሰዎች ጣልቃ በመግባት ምናልባት መንገድ ሊጠቁሙ ይችሉ እንደሆን እንጂ ችግሩን ሊፈቱት እንደማይችል እሙን ነው፡፡
ትዳርን በትክክለኛው እና በጣፈጠ መንገድ ለመምራት ፍቅር ዋናው መሰረቱ ነው፡፡ ማፍቀር ሲባል ደግሞ አንዱ አፍቃሪ ለሌላው ከልቡ በትክክለኛው መንፈሱና አስተሳሰቡ መሆን አለበት፡፡ የብዙዎች ትዳር ውድቀት እነዚህን ነገሮች ካለማወቅ ወይንም ካለማሰብና ካለመተግበር የሚመጣ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ተጋቢዎች አንቺ ትብሽ አንተ ትብስ ከመባባል ፈንታ ስለየራሳቸው ፍላጎትና አስፈላጊ ነገሮችን ስለማሟላት ማሰብ በሚጀምሩበት ወቅት በተከታይ የትዳራቸውን መውደቅ ጅማሬ ማየት ይሆናል፡፡
ተጋቢዎች በእርስ በርስ ግንኙነታቸው ላይ ችግር እንዳይፈጠር አንዳቸው የሌላውን ስሜት መረዳት፤ ፍላጎትን ማወቅ እና መተግበር ፤የራስ ወዳድነትን በማስወገድ መተሳሰብን፤ መፋ ቀርን ከልባቸው ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ስለዚህም ነው ትዳር ቁልፉ በሁለቱ ተጋቢ ሰዎች እጅ እንጂ በሌላ ሰው እጅ አይደለም የሚባለው፡፡ ይህንን የተረዱ ባልና ሚስት የግል ፍላጎትን ብቻ ከማንጸባረቅ ተቆጥበው የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን በማሻሻል አንዳቸው በአን ዳቸው ላይ የሚኖራቸውን ብስጭትና ቁጣ በመተው አብረው ጥሩ ጊዜን በማሳለፍ ትዳራቸውን በሰመረ መልክ ለመምራት ይችላሉ፡፡ በእርግጥ የተበላሸን ነገር ለማስተካከል በአንድ ምሽት የሚ ሰራ ነገር የለም፡፡ ትዳር የባልና ሚስቱ ብቻ ሳይሆን በጋራ የሚያፈሩዋቸው ልጆች፤ በዙሪያው ያሉ ቤተሰቦች፤ የሚያፈሩት ሀብት እና መሰል ጉዳዮችን አብሮ የያዘ እንደመሆኑ ለማስተካከል ጊዜ መፈ ለጉ አይቀርም፡፡
ትዳር እንዲሰምር ሁለቱ ተጋቢዎች ማለትም ባልና ሚስቱ ተከታዮቹን የምሁራን ምክሮች ልብ ሊሉአቸው ይገባል፡፡
እምነትና ፍቅር የተሞላው ጉዋደኝነት፤
ይህ በተቀዳሚነት ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ነው። ምክንያቱ ደግሞ ለማንኛውም ግንኙነት መሰረት ስለሆነ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የሚያልፉ ጉዋደኛሞች መቀራረባቸው ይጨምራል፤ አንዳቸው አንዳ ቸውን ቀኑን እንዴት እንዳሳለፉ…ምን እንዳጋጠማቸው ይጠያየቃሉ። ጉዋደኛ ሞቹ አንዳቸው ለሌላው ደግነት በተሞላው መንገድ በግልጽ እና ክብር በመስጠት ሊቀራረቡና አንዳቸው ከሌላው የሚጠብቁትን ዝቅ አድርገው እራሳቸው ለሌላው የትዳር ጉዋደኛ ማድረግ የሚገባቸውን ግን ከፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡  
እኩልነት፤
ምንም እንኩዋን ባልና ሚስት ለግንኙነታቸው ምክንያት የሚሆኑ የተለያዩ ጥንካሬዎችን፤ ዋጋዎች፤ አስተያየቶችን፤ አስተዋጽኦዎችን ቢያደርጉም የዚህ ሁሉ ውጤት በሁለቱም ላይ እኩል መሆኑን መቀበል ግድ ነው፡፡
ድጋፍ ማድረግና ማበረታታት፤
ሴትም ትሁን ወንድ የትዳር ጉዋደኛ ሲመርጡ የህይወትን መንገድ አብሮ ለመጉዋዝ ቃል መግ ባት አብሮ መኖሩን መርሳት አይገባም፡፡ በዚህ ኃላፊነት ውስጥ ሁለቱም አንዳቸው ለሌላኛው ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። አንዳቸው አንዳቸውን በማበረታት ረገድም አንዳ ቸው ለሌላኛው ተቃራኒ በመሆን ሳይሆን በመግባባት፤ በማበረታ ታት ላይ የተመሰረተ ድርጊት እንዲፈጽሙ ይጠበቃል፡፡
ማነጻጸር፤
የትዳር ጉዋደኛሞች አንዱ የሚያነሳውን ሀሳብ ሌላኛው ለመቀበል ዝግጁ መሆን ይጠበቅባ ቸዋል፡፡ ለሚነሳው ሀሳብ ጥሩ ግምት እና ዋጋ መስጠት እና የእራስንም ሀሳብ በትህትና ያለ ተቃርኖ ስሜት መግለጽ ትክክል ነው፡፡ በዚህ መሀልም ከሁለቱም ወገን የቀረበውን ሀሳብ አይተው ወደሚያስታርቃቸው መንገድ መዝለቅ የሁለቱ ተጋቢዎች ግዴታና ኃላፊነት ነው፡፡
የስነልቡና አማካሪዎች እንደሚሉትም ትዳርን ስኬታማ እንዲሆን ቁልፉን በእጃቸው የያዙ ሁለቱ ተጋቢዎች ሊፈጽሙት ከሚገባቸው ተጨማሪ ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
ትዳርን በአንድ ጥግ ወይንም ቦታ እንደሚቀመጥ የተተወ እቃ አድርጎ ማሰብ አይገ ባም፡፡ ምንጊዜም ሊስተካከል የሚችልበትን መንገድ ሁለቱም ተጋቢዎች ሳያሰልሱ ሊያስቡበት እና በመግባባት ሊፈጽሙት ይገባቸዋል፡፡
በትዳር ጉዋደኛ ለአንተ ወይንም ለአንቺ ሊደረግልሽ ወይንም ሊደረግልህ የሚገባውን ነገር ለትዳር ጉዋደኛህ ወይንም ጉዋደኛሽ አድርጊ ወይንም አድርግ። እንዴት ማናገር ወይንም እርዳታ ማድረግ እንደሚገባ ሁልጊዜም እራስን መጠየቅ ይገባል፡፡  
በመካከል ያለውን ልዩነት መቀበል እና የትዳር ጉዋደኛ ማለት በትክክል የእራስ ቅጂ ሊሆን እንደማይገባው በማመንም አክብሮ ኑሮን በጣመ መንገድ መቀጠል ይገባል፡፡ ልዩነትን ከማጉላት ወይንም ከማሰብ ይልቅ ተመሳሳይ የሆኑ ነገሮችን በማሰብ ማድነቅ ይጠቅማል።
ጥብቅ የሆነ ግንኙነት ወይንም ጉዋደኝነት ለትዳር ይጠቅማል፡፡ እንደጉዋደኛ ቅርርብ መፍጠር አብሮ መሆንን መዝናናትን አንዱ ለአንዱ እንዲያስብ ማድረግን ሊያመጣ ይችላል፡፡
የትዳር ጉዋደኛን ለመውደድ ገደብ ሊኖረው ወይንም ከዚህ በመለስ ማለት አይጠበቅም፡፡
አንዱ ከሌላው ይህንን እፈልጋለሁ የሚል ነገር ሳይኖር መዋደድ ለተጋ ቢዎች ያስፈልጋል፡፡ በኑሮአቸው ዘመን አንዳቸው አንዳቸው ላይ ግዴታ መጣል ወይንም ይህ ያንተ/ያንቺ ድርሻ እንጂ የእኔ አይደለም በሚል ስሜት ሊነጋገሩ አይገባም፡፡
እውነተኛ ፍቅር መጠኑ ይህን ያህል ተብሎ ባልየው ይህን ያህል ወደደ ወይንም ሚስትየው የወደደችው በዚህን ያህል ነው ተብሎ ቀመር የሚወጣለት አይደለም፡፡ በባልና ሚስት መካከል መደረግ የሚገባው ነገር ስለሆነ ፍቅር አንዳቸው ለሌላቸው ይተረጎማል፤በስራ ላይ ይውላል፡፡
እውነተኛ ፍቅር ወደው እንጂ ተገድደው የሚፈጽሙት አይደለም፡፡ ስለዚህ ተጋቢዎች ትዳር ከመመስረታቸው በፊት ማሰብ ይጠቅማቸዋል፡፡

Read 9580 times