Monday, 10 September 2018 00:00

ቡና አቅራቢዎች ለወደመባቸው ንብረት መንግስትን 150 ሚ. ብር ካሣ ጠየቁ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)


     በምዕራብ ጉጂ ዞን ተፈጥሮ ከነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ “የቡና ኢንቨስትመንታችን ወድሞብናል፣ አሁንም ወደ ስራ መመለስ አልቻልንም” ያሉ ባለሃብቶች፤ መንግስትን 150 ሚሊዮን ብር ካሣ መጠየቃቸው ታውቋል፡፡
27 ባለሃብቶች ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ፤ ቡና አጥቦ ለገበያ በማቅረብ ኢንቨስትመንት በአካባቢው ለረጅም ዓመታት ተሰማርተው መቆየታቸውን ጠቅሰው፤ ከወራት በፊት በጉጂና በጌዲኦ ተወላጆች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ተከትሎ የቡና ማጠቢያና ማበጠሪያ ማሽኖቻቸው ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ጠቁመዋል፡፡ የወደመባቸው ንብረት ጠቅላላ ግምቱ 150 ሚሊዮን ብር ገደማ መሆኑን የጠቀሱት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፤ መንግስት ተገቢውን ካሣ እንዲከፍላቸው ጠይቀዋል፡፡ ከካሣ ጥያቄው ባሻገርም ወደ ኢንቨስትመንት ስራቸው መመለስ እንዲችሉ መንግስት አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ተማፅነዋል - በጽሁፍ ባቀረቡት አቤቱታ፡፡

Read 3172 times