Tuesday, 18 September 2018 10:32

ኤችአይቪ በኢትዮጵያ…ዛሬም ትኩረት ይሻል

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)


    ኤችአይቪ ኤይድስ በኢትዮጵያ እንደገና ምልከታን ይሻል የሚለው October 06/2017 ከወጣው የአዲስ ስታንዳርድ ድረገጽ የተገኘ ነው፡፡ መረጃው ኤችአይቪ ኤይድስ በኢትዮጵያ ምን ሁኔታ ላይ ይገኛል የሚለውን ለንባብ ዘርዘር አድርጎ እንደሚከተለው አቅርቦአል፡፡
ባለፉት ሶስት አስርት አመታት በኢትዮጵያ በኤችአይቪ ኤይድስ ምክንያት ለሕልፈት የተዳረ ጉትን ሰዎች ምን ያህል እንደሆኑ ሲታሰብ እጅግ ከባድ መሆኑን የሚያሳይ በኢትዮጵያ ፌደራ ላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኤችአይቪ ኢይድስ መከላከልና ቁጥጥር ቢሮ (FHAPCO) እንዳ መለከተው በአማካ በየአመቱ 19‚743/ሰዎች በየአመቱ ይሞቱ እንደነበርና በዚህም ምክንያት 247‚250/ ልጆች ካለወላጅ ይቀሩ እንደነበር ያመለክታል፡፡
የ(FHAPCO) መረጃ እንደሚያመለክተው በ1984/ዓ/ም ኤችአይቪ ኤይድስ በኢትዮጵያ በመ ላው ሀገሪቱ በስፋት የተስፋፋና በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የሚሊዮኖችን ሕይወት አደጋ ላይ የጣለ እንደነበር አይዘነጋም። ምክንያት ተደርገው ከሚወሰዱትም ምክ ንያቶች መካከል የንቃተ ሕሊና ማነስ እና በሌሎች የአፍሪካ እና የኤሽያ አገራት የታዩ ልምዶች ናቸው፡፡  
የአለም የጤና ድርጅት እንዳወጣው መረጃ እስከ 2016/መጨረሻ ድረስ በአለም ላይ ከ70/ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኤችአይቪ ኤይድስ ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ 35/ሚሊዮን የሚሆኑት በኤችአይቪ ኤይድስና ተያያዥ ምክንያቶች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት ወደ /36.7/ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ይህም በአለም ላይ አስከፊው ገጽታ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ያለውን ገጽታ (FHAPCO) ሲገልጸው ወደ /718.550/ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሲሆን በመቶኛ ሲታይ ወደ 1.18% ይሰላል፡፡ ይህ ደግሞ በአገሪቱ ኤችአይቪ አደገኛ መሆኑን እና እንደገና ትኩረት የሚሻ መሆኑን ይጠቁማል፡፡
እንደውጭው አቆጣጠር በ2016/ በኢትዮጵያ የተሰራው Demographic Health Survey (DHS) እንደሚያሳየው በቅኝቱ ከተካተቱት ወደ 56% የሚሆኑ ሴቶች እና 55% የሚሆኑ ወንዶች ስለ ኤችአይቪ ምንም አይነት ምርመራ አድርገው እንደማያውቁ የሚያሳይ ሲሆን ምናልባትም መላው ህዝብ ምርመራውን ቢያካሂድ ኖሮ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች ቁጥር በዚህ ይወሰን ይሆን? ወይንስ? የሚለውን ጥያቄ ያጭራል። ምርመራ አርገው ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው መኖሩ ከተነገራቸው ውስጥ 72% የሚሆኑት አምነው ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ ለራሳቸው ቃል የገቡ ሲሆን ወደ 28% የሚሆኑት ግን ቫይረሱ በደማቸው መኖሩን አውቀውም ምንም እርምጃ የማይወስዱ እና የጤና ችግር እንደገጠማቸው አድርገው እንደማይወስዱትም መረጃው ይጠቁማል፡፡  
አዲስ ስታንዳርድ እንዳስነበበው በበ1990/ዎቹ እና 2000/ዎቹ ዓ/ም በኤችአይቪ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በርከት ያለ እንደነበርና በሆስፒታል አልጋ ከያዙ ሕመምተኞች መካከልም 1/3ኛ የሚሆ ኑት ግማሽ ያህሉ ተመርምረው በደማቸው ውስጥ ቫይረሱ የተገኘ መሆኑን ይጠቁ ማል፡፡  
በ2030/ እንደውጭው አቆጣጠር ኤችአይቪ ኤይድስ ስርጭቱ በቁጥጥር ስር እንደሚውል ሀገ ራት በአለም አቀፍ ደረጃ ቃል የገቡበት መሆኑ እሙን ነው፡፡ በቅርብ የተገኘው መረጃ እንደሚ ጠቁመው በአፍሪካ 5/ሀገራት ማለትም ሌሶቶ፤ማላዊ፤ስዋዚላንድ፤ዛምቢያ፤ እችአይቪ ኤይድስን በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ ለውጥ እያስመዘገቡ ሲሆን ኢትዮጵያም ወደእዚህ ስኬት ለመድረስ ገና ብዙ ስራ እንደሚቀራት ሁኔታዎች ያመላክታሉ፡፡
የኤችአይቪ ኤይድስ ቫይረስ ስርጭት ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ ከፍ ብሎ ይታያል፡፡ በኢትዮጵያ ኤችአይቪ በደማቸው ካለባቸው ሰዎች ውስጥ 39% የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ ሴቶች ግን ወደ 61% ያህል ናቸው፡፡ ከእነዚህም 25% የሚሆኑት በሴተኛ አዳሪነት ስራ የተሰማሩ ናቸው፡፡
እንደ FHAPCO መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2009/ዓ/ም 27.288 የሚሆኑ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው መኖሩ ተረጋግጦአል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 16.021/ ማለትም 59% የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ ወንዶች ደግሞ 11.267/ 41% ናቸው፡፡ በእርግዝና ላይ ካሉት ከ/3/ሚሊዮን ሴቶች መካከል ወደ /27.000/የሚሆኑት ቫይረሱ በደማቸው ተገኝቶአል፡፡
እንደ መረጃው እማኝነት ሴቶች ይበልጡኑ በኤችአይቪ ቫይረስ የመጠቃታቸው ምክንያት (ብቸኛው) ባይሆንም በኢትዮጵያ ወንዶች በኢኮኖሚው ተጽእኖ ስለሚያደርጉ እንዲሁም ሴቶች እውቀታቸውን በሚያዳብሩባቸው ፕሮግራሞች ላይ መገኘት አለመቻላቸው እና የወሲብ ግንኙነቱ ባህርይ ይጠቀሳል፡፡ ከአንድ በላይ የወሲብ ጉዋደኛ ማፍራት የተለመደ በመሆኑም አንድ ወንድ ከአንድ በላይ ከሆኑ ሴቶች ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ሊፈጽም ስለሚችል የቫይ ረሱን ስርጭት በሴቶች ላይ ከፍ እንዲል ያደርገዋል። ይህ አይነቱ ድርጊት በሴቶች ላይ ያልተ ለመደ በመሆኑ ወንዶቹ በሴቶች ቁጥር ልክ የቫይረሱ ተጎጂዎች እንዳይሆኑ ያደርጋል፡፡ ሴቶች በጾታ (Gender) ጀንደር ስርአቱ በተሳሳተ መንገድ ምልከታ የሚደረግባቸው በመሆኑና መብታ ቸውን ለማስከበርም አቅም የሚያጡ በመሆኑ እንዲሁም በወንዶቹ ፍቃድና ውሳኔ የሚንቀ ሳቀሱ በመሆኑ ኤችአይቪ ኤይድስን ለመከላከል በሚያስችሉ ፕሮግራሞች ላይ የመገኘት እድላ ቸው ጠባብ ነው፡፡  ከዚህም በተጨማሪ ብዙዎቹ ሴቶች ከባሎቻቸው ጋር ሊኖራቸው የሚገባውን የወ ሲብ ግንኙነት በተመለከተ እና የጤና አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችላቸው ምንም አይነት ውይይት የማድረግ እድል የላቸውም፡፡
ጾታዊ ጥቃት ሌላው ሴቶችን ለኤችአይቪ ቫይረስ ለመጋለጥ እድል የሚከፍት መጥፎ አጋጣሚ ነው። እንደውጭው አቆጣጠር በ2016/ የተደረገው የDHS ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከጠ ቅላላው ጾታዊ ጥቃት መካከል 7% የሚሆነው ወሲባዊ ጥቃት እንደነበረ እና በጥናቱ ከተካ ተቱት 10/ሴቶች አንዱዋ ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባት መሆንዋ ተረጋግጦአል፡፡ ሪፖርቱ አክሎ እንዳወጣውም ትዳራቸው የፈረሰ ወይንም በተለያዩ ምክንያቶች ብቻቸውን የሚኖሩ ሴቶች በጋብቻ ላይ ካሉት ይበልጡኑ ተጎጂዎች ሆነው ተገኝተዋል፡፡
የኤችአይቪ ስርጭትን በተመለከተ አዲስ አበባ ላይ የሚታየው የኤችአይቪ ኤይድስ ስርጭት በኢትዮጵያ ካሉ ሌሎች ከተሞች ይበልጥ መሆኑ የFHAPCO መረጃ ይጠቁማል ሲል አዲስ ስታንደርድ ለንባብ ብሎታል፡፡ በአዲስ አበባ ይኖራሉ ተብለው ከሚጠቀሱት 4/ሚሊዮን ሰዎች ወደ 5/% በጋምቤላ 4/% በሐራር እና ድሬ ደዋ 2.9/% ስርጭት እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በአዲስ አበባ ብዙዎቹ ነዋሪዎች ስለኤችአይቪ ኤይድስ ፕሮግራሞች ንቃተ ሕሊና ቸው የዳበረ እና ስለሕመሙ እውቀት አላቸው እንዲሁም ጤናቸውን ለመጠበቅ የተሟላ የጤና አገልግሎት በቅርብ ሊያገኙ ይችላሉ ቢባልም የቫይረሱ ስርጭት ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ መኖሩ ታውቆአል፡፡
ከአሁን ቀደም WHO ኤችአይቪ ኤይድስን በሚመለከት ለንባብ ያለውን መረጃ በዚህም እትም ለንባብ ብለነዋል፡፡
የአለም የጤና ድርጅት በአለም አቀፍ ደረጃ ኤችአይቪን ስለመከላከል ያወጣው ቁልፍ መልእክት፡-
ከኤችአይቪ ኤይድስ ጋር በተያያዘ የማንም ሰው ጉዳይ ቸል ሊባል አይገባውም፡፡
ኤች አይቪ የሳንባ በሽታ እና ሄፒታይተስ ለተባሉት ሕመሞች ከሚሰጠው አገልግሎት ጋር የተቀናጀ ነው፡፡
ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ለሚገኝባቸው ሰዎች የሚሰጠው አገልግሎት ከፍተኛ ጥራት ያለው መሆን አለበት፡፡
የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ሰዎች በሚችሉት መንገድ ደህንነታቸውን መጠበቅ እንደሚችሉ ሊያውቁ ይገባል፡፡
ኤችአይቪን በሚመለከት ያለው ምላሽ በጎ እና ጠንካራ የጤና አጠባበቅ ዘዴ እንዲኖር ማድረግ ያስችላል፡፡

Read 2468 times