ሚዩዚክ ሜይ ዴይ ከኢትዮጵያ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነገ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ-መፃህፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ በአርክቴክት ሚካኤል ሽፈራው “የሞሮኮ አገር እውነት” መፅሐፍ ላይ ውይይት ያካሂዳል፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት ገጣሚና ጋዜጠኛ ዮሐንስ ገ/መድህን ሲሆኑ መድረኩም በሰለሞን ተሰማ ጂ እንደሚመራ ታውቋል፡፡
ደራሲው አርክቴክት ሽፈራውም በፕሮግራሙ ላይ የሚታደም ሲሆን፤ በውይይቱ ላይ ፍላጐት ያለው እንዲሳተፍ አዘጋጁ ጋብዟል፡፡