Saturday, 15 September 2018 00:00

“የወፍ ጐጆ ምህላ” ነገ ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የገጣሚ፣ ተወዛዋዥና ኬሮግራፈር ኤፍሬም መኮንን (ኤፊማክ) ሁለተኛ ሥራ የሆነው “የወፍ ጐጆ ምህላ” የግጥም መፅሐፍ፣ ነገ ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ ናዝሬት አዳማ በሚገኘው ተስፋዬ ኦሎምፒክ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በስነ ስረዓቱ ላይ ገጣሚያን አዳም ሁሴን፣ ሰለሞን ሳህለና በላይ በቀለ ወያን ጨምሮ በርካታ ገጣሚያን ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ከመፅሐፉ የተመረጡ ግጥሞችም ይነበባሉ ተብሏል፡፡ “ፍራሽ አዳሽ” የተሰኘ የአንድ ሰው ተውኔት በተስፋሁን ከበደ ለታዳሚ እንደሚቀርብም ገጣሚ ኤፍሬም መኮንን ገልጿል፡፡
“ግጥም በውዝዋዜን” ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረክ ያስተዋወቀው ኤፍሬም፤ ነገም ግጥምን በውዝዋዜ ለታዳሚ እንደሚያቀርብ አስታውቋል፡፡ የግጥም መፅሐፉ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ 61 ግጥሞች ያሉት ሲሆን፤ በ94 ገጾች ተቀንብቦ በ-------------- ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ገጣሚው ከዚህ ቀደም “ለባለ ቅኔው ቅኔ አጣሁለት” የተሰኘ የግጥም መፅሐፍ በግሉ ያሳተመ ሲሆን፤ “ሰሚ ያጡ ብዕሮች” እና “የግጥም ከተራ” የተሰኙ የግጥም መፅሐፎችን ከሌሎች ገጣሚዎች ጋር በጋራ አሳትሞ ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡


Read 2466 times