Saturday, 15 September 2018 00:00

የአንዷለም አራጌ “በዘመናት መካከል” ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በቅርቡ ከእስር የተለቀቀው የታዋቂው ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ “በዘመናት መካከል” የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ እንደሚመረቅ የምርቃቱ አዘጋጅ ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አስታወቀ፡፡
መጽሐፉ አንዷለም ከእስር ቤት ገጠመኙ እስከ ወቅታዊው የአገሪቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ በጥልቀት የሚያስቃኝበት ነው፡፡ በምርቃቱ ላይ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረትና የሕግ መምህርና ጠበቃ ጌዲዮን ወ/ዮሐንስ ስለ መፅሐፉ አስተያየታቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ የምርቃት ሥነ ሥርዓቱ በግጥም፣ በወግና በባህላዊ ሙዚቃ እንደሚታጀብ ታውቋል፡፡ በ308 ገፅ የተቀነበበው መጽሐፉ በ160 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ከዚህ ቀደም “ያልተኬደበት መንገድ” እና “የአገር ፍቅር እዳ” የተሰኙ መጽሐፎችን ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡  

Read 3792 times