Saturday, 15 September 2018 00:00

ኖህ ሪል እስቴት ነገ “ኢስት ጌት” የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ያስረክባል

Written by  መንግስቱ አበበ
Rate this item
(2 votes)

  “ያልተገነባ አንሸጥም” በሚል መርህ የሚታወቀው ኖህ ሪል እስቴት፤ ነገ በሲኤምሲ አካባቢ ኖህ ኢስት ጌት በማለት የሰየማቸውን ባለ ሰባት ወለል፣ 120 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ ከትናንት በስቲያ በቤስት ዌስተርን ሆቴል በሰጠው መግለጫ፤ በአንድ ዓመት ተኩል የገነባቸውን ቤቶች እንደሚያስመርቅ ጠቅሰ፤ ቤቶቹ በለአንድ ወለል፣ ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታ ቤቶች እንደሆኑ ገልዷል፡፡
ከተመሠረተ 6 ዓመት ያስቆጠረው ኖህ ሪል ኢስቴት፤ እስክ አሁን ድረስ ከ3‚500 በላይ አፓርትመንቶች፣ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማት ገንብቶ፤ ለአገር ውስጥ ደንበኞች ወይም ለኢትዮጵያውያን ዳያስፓራዎች ማስረከቡን ገልፆ፤ በ2010 ዓ.ም 1‚900 ቤቶች  መገንባታቸውን፣እንዲሁም በውጭ አገር ለሚኖሩ ኢትየጵያውያን እስከ 20 ዓመት የሚደርስ ብድር ለማመቻቸት ከባንኮች ጋር  እየሠራ መሆኑን አሰታው፡፡
ኖህ ሪል እስቴት በውጭ  ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን 10 በመቶ ቅናሽ ለማድረግ ማቀዱን ጠቁም፤ በያዝነው 2011 ዓመት ተጨማሪ 5 ኘሮጀክቶች እንደሚያስረክብም አስታውቋል፡፡
ሥራዬን እስከ ማቆም ያስገደደኝ ችግር አላጋጠመኝም ያለው ኖህ ሪል እስቴት፤ ነገር ግን የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ የቆጣሪ፣ የትራንስፎመር፣ የመሬት አቅርቦት፣ የሠለጠነ የሰው ኃይል እጥረት፣ መንግሥት ለሪል እስቴቶች የሚያርጋው ድጋፍ አናሳነት ካጋጠሙን ችግሮች ጥቂቱ ናችው ብሏል።
ከደንበኞች በየጊዜው በሚቀርብልን ጥያቄ መሠረት፤ የኪራይ ቤቶች አመቻችተናል ያለውድርጅቱ፤ ከባንክ ጋር በማገናኘት በረዥም ጊዜ የሞርጌጅ ብድር ደንበኛው ቤቱን የሚገዛበት ሁኔታም ይመቻችል ብሏል፡፡
ሕንፃውን ሠርቶ አሰረክቦ መወጣት ብቻ ሳይሆን የውሃ፣ የመብራት፣ የፅዳት፣ የጥገና፣ የደህንነት አገልግሎት የሚሰጥ የሕንፃ አስተዳደር (አሴት ማኔጅመንት) ማቋቋሙንም ኖህ ሪል እስቴቱ አስታውቋል፡፡


Read 2997 times