Print this page
Saturday, 29 September 2018 14:46

“የጥበብ አሻራ” የስዕል ኤግዚቢሽን ማክሰኞ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ሰዓሊ ተፈሪ ተሾመ በርካታ ሥራዎች ለእይታ የሚቀርቡበት “የጥበብ አሻራ” የስዕል ኤግዚቢሽን የፊታችን ማክሰኞ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በጀርመን የባህል ማዕከል (ገተ) በገብረክርስቶስ ደስታ አዳራሽ እንደሚከፈት የአርቲስቱ ጓደኞች አስታወቁ፡፡
ለቀጣዮቹ 15 ቀናት ለእይታ ክፍት ሆኖ በሚቆየው በዚህ የሥዕል ኤግዚቢሽን ላይ በሠዓሊዎቹና በስራዎቹ ላይ ውይይት እንደሚካሄድ፣ በጓደኞቹ በተሰራለት ሀውልት ሥር በሚቀመጥ መዝገብ ጐብኚዎች ስለ አርቲስቱ ያላቸውን ስሜት እንዲያሰፍሩ እንደሚደረግና ስለ አርቲስቱ ህይወትና ሥራ የሚገልፅ ቡክሌት ለጐብኚዎች እንደሚሰራጭ የአርቲስቱ የቅርብ ጓደኛና ቤተሰብ የሆነው ከያኒ ፈለቀ የማር ውሃ አበበ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
‹‹አርቲስቱ ህይወቱን ሙሉ መኖሪያውንም ስራውንም ስቱዲዮው ውስጥ አድርጐ ለሙያው የኖረ ትልቅ የጥበብ ሰው ነው ያለው ከያኒፋለቀ፤ ትልቅ ችሎታ እያላቸው ባልተመቻቸ ህይወትኑሮ ውስጥ ህይወታቸውን የሚገፉ ሰዎች መገለጫ ነው›› ብሏል፡፡ ጓደኞቹን አመስግኗል፡፡ የአርቲስቱን ህይወትና ሥራ የሚዘክር ዘጋቢ ፊልም በጓደኞቹ እየተሰራ ሲሆን መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም በአርቲስቱ የልደት ቀን ለእይታ ይቀርባል ተብሏል፡፡

Read 3290 times