Print this page
Saturday, 29 September 2018 14:45

ሰምና ወርቅ 10ኛ የጥበብ ሳምንቱን ሀሙስ ያካሂዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይንመንት 10ኛ የኪነ-ጥበብ ምሽቱን የፊታችን ሀሙስ  ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ መገናኛ ፓኖሮማ ሆቴል ጐን በሚገኘው ቫምዳስ የመዝናኛ ማዕከል ያካሂዳል፡፡
በምሸቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ዶ/ር ሰሎሞን በላይ፣ ዶ/ር መንበረ አክሊሉ፣ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ ኡስታዝ አብዱል ሰላም ሰኢድ፣ አርቲስት ባዩሽ አለማየሁ፣ አርቲስት አዜብ ወርቁ፣ አርቲስት ፍቃዱ ከበደ፣ ደራሲና ወግ አዋቂ በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር፣ ገጣሚያኑ ሚካኤል ምናሴና ሄለን ፋንታሁን ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡና ዝገጅቱም በመሶብ ባህላዊ ባንድ እንደሚታጀብ የፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው አለሙ ገልጿል፡፡

Read 4290 times