Print this page
Saturday, 06 October 2018 10:09

የፊልምና የቲያትር ቅድመ ምርመራ (ሳንሱር) እንዲቀር ተደረገ

Written by  መታሰቢያ ካሣዬ
Rate this item
(0 votes)


 በፊልምና ቲያትር ሥራዎች ላይ ይደረግ የነበረው ቅድመ ምርመራ (ሳንሱር) ከትናንት ጀምሮ እንዲቀር መደረጉ ተገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ ፊርማ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፤ ከዚህ ቀደም በፊልምና በግል ቲያትር ሥራዎች ላይ ይደረግ የነበረው ቅድመ ምርመራ ከመስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቀር ተደርጓል፡፡
ቀደም ሲል ይሰሩ የነበሩ ፊልሞችና ቲያትሮች ለህዝብ ከመቅረባቸው በፊት ቅድመ ምርመራና ግምገማ ይደረግባቸው እንደነበር ያስታወሰው ይኸው ደብዳቤ፤ ሲኒማ ቤቶችንም ለማሳየትና ለማሰራጨት ቢሮው ከግምገማ በኋላ የሚሰጠውን ማስረጃ ይጠይቁ እንደነበር ገልጿል፡፡
ይሁንና ይህ አሰራር የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 29ኝን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትንና ቅድመ ምርመራ የተከለከለ መሆኑን የሚገልፀውን ሃሳብ የሚጣረስ በመሆኑና ግምገማው ወጥነት በሌለው ሁኔታ በፊልምና በቲያትር ሥራዎች ላይ ብቻ ያተኮረ በመሆኑ እንዲቆም መደረጉ ታውቋል፡፡


Read 982 times