Saturday, 06 October 2018 11:07

“ድሮና ዘንድሮ” የመፅሐፍት አውደ ርዕይ ለሳምንት ይቆያል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ማክሰኞ በብሔራዊ ቴአትር አርት ጋለሪ የተከፈተው “ድሮና ዘንድሮ” የተሰኘው የመፅሐፍት አውደ ርዕይ እስከ መጪው ሳምንት አርብ  ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል፡፡ በስድስት የመፅሐፍት መደብር ባለቤቶች በተዘጋጀው በዚህ አውደ ርዕይ ላይ የድሮና ከገበያ የጠፉ መፅሐፍት፣ ጋዜጦች፣ መፅሔቶች፣ የሩሲያ ልቦለዶች፣ የድሮና ዘንድሮ የትምህርት መፅሐፍት ለዕይታና ለሽያጭ መቅረባቸውን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡ በአውደ ርዕዩ ላይ መጽሐፍት  ለሚገዙ ጎብኚዎች፤ የ20፣ 30 እና 50 በመቶ ቅናሽ እንደሚደረግም ተጠቁሟል፡፡     

Read 919 times