Saturday, 06 October 2018 11:13

“ኢትዮጵያዊነት፣ ኢኮኖሚያዊ ልማትና እንቆቅልሾቹ” ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ አበበ ኃብተሥላሴ የተጻፈውና አዲሱ የለውጥ ጉዞን አቅጣጫ የሚያመላክተው “ኢትዮጵያዊነት፣ ኢኮኖሚያዊ ልማትና እንቆቅልሾቹ” የተሰኘ መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
መፅሐፉን ለመፃፍ ያነሳሳቸው፣ በምርጫ 97 የተፈፀመው የህዝብ “የሚመራኝን እመርጣለሁ” እና የአገዛዙ የድምፅ መስረቅና የህዝብን ድል የመቀልበስ ድርጊት እንደሆነ በመግቢያቸው የጠቆሙት ደራሲው፤ በወቅቱ ስለ ህወሓት/ኢህአዴግ ልማታዊ መንግስትነት የቀረቡ ፅሁፎች ህዝብን የተሳሳተ እሳቤ እንዲይዝ ያደረገ በመሆኑ፣ ይህንን የተሳሳተ እሳቤ ለማስተካከልና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች፣ ተጨማሪ ፅሁፍ እንዲያቀርቡ ለማነሳሳት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
ስለ ስልጣኔ አካሄድ በኢትዮጵያ፣ ስለ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ ስለ ልማታዊ መንግስትና ምንነትና ተያያዥ ጉዳዮች በስፋት የሚዳስሰው መፅሐፉ፤ በአራት ክፍሎች፣ በሰባት ምዕራፎችና በ216 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ100 ብር እና በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ መጽሐፉን ክብሩ መፅሐፍት መደብር እንደሚያከፋፍለው ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 4600 times