Saturday, 06 October 2018 11:14

“ለኢትዮጵያ አንድነት የተከፈለ የደምና የአጥንት ዋጋ” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ ደርቤ መንግስቱ የተፃፈውና በወቅቱ የአገሪቱ የለውጥ ሂደት ላይ የሚያጠነጥነው “ለኢትዮጵያ አንድነት የተከፈለ የደምና የአጥንት ዋጋ” የተሰኘ መጽሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
መፅሐፉ ከ20 አመታት መለያየት በኋላ በወረደው ሰላም ዳግም ስለተገናኙት የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች፣ ባልተፈፀመ ታሪክ ጥላቻን በመንዛት፣ በአማራና ኦሮሞ ወንድማማች ህዝቦች ላይ ተፈጥሮ ስለነበረው ግጭትና ግጭቱ ስለተፈታበት መንገድ እንዲሁም ለአገር አንድነት ሲባል ስለተከፈለ መስዋዕትነት በጥልቀት ይዳስሳል።
ለአገራቸው ደምና አጥንት የከፈሉ ጀግኖችን ክብርና ሞገስ የሚሰጠው መጽሐፉ፤አንዳንዶቹን በፎቶግራፍ ጭምር በማስደገፍ ለመዘከር ይሞክራል፡፡ መጽሐፉ በ291 ገጾች የተቀነበበ ሲሆን በ160 ብር ይሸጣል፡፡

Read 4768 times