Saturday, 13 October 2018 09:17

የተሻሻለው የበጎ አድራጎቶች ማህበራት አዋጅ፤ የድርጅቶችን ነፃነት የሚያስጠብቅ ነው ተባለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

ገንዘብ ከማንኛውም ህጋዊ ምንጭ እንዲያሰባስቡ ይፈቅዳል

ማህበራትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤ ከየትኛውም ህጋዊ ምንጭ ገንዘብ መሰብሰብ የሚያስችላቸው አዲስ ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀ ሲሆን አዋጁ የድርጅቶችን ነፃነት የሚያስጠብቅ ነው
ተብሏል፡፡በጠቅላይ አቃቤ ህግ ስር የተቋቋመው የፍትህና የህግ ማሻሻያ ምክር ቤት፤ በ2001 ዓ.ም የወጣውና ለበርካታ ማህበራትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መዳከም ምክንያት ሆኗል
በሚል ሰፊ ትችት ሲቀርብበት የነበረውን አዋጅ አሻሽሎ እንዳጠናቀቀ ታውቋል፡፡
አዲስ በተዘጋጀው ረቂቅ ላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (ማህበራትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች) በፈለጉት ጉዳይ ላይ የመስራትና የመንቀሳቀስ መብታቸው ያለምንም ገደብ መጠበቁ
ተጠቁሟል፡፡ ከዚህ ቀደም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከውጪ የሚያገኙት ገንዘብ ከ10 በመቶ መብለጥ እንደሌለበትና በዋናነት ገቢያቸው ከሀገር ውስጥ እንዲሆነ የሚያስገድደው አንቀፅም ሙሉ
ለሙሉ ተሻሽሎ ድርጅቶች ከየትኛውም ህጋዊ ምንጭ ገንዘብ ማሰባሰብ እንዲችሉ ይፈቅዳል ተብሏል፡፡
ይህን አዋጅ አስመልክቶም ከትናንት በስቲያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
አዲሱ የተሻሻለው ህግ፤ በሀገሪቱ የተጀመረውን የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታን ተቋማዊ ለማድረግ በእጅጉ ይረዳል ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡Read 1866 times