Print this page
Saturday, 13 October 2018 10:26

“ስውር መፈንቅለ መንግሥትና የዐቢይ ቀጣይ ስጋቶች” ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

በደራሲ እያሱ ገብረመስቀል የተጻፈው “ሥውር መፈንቅለ መንግስትና የዐቢይ ቀጣይ ስጋቶች” የተሰኘው መፅሐፍ ባለፈው ሳምንት ለንባብ በቅቷል፡፡ ከዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሲመት ማግስት የተከሰቱትን አጠቃላይ የፖለቲካ ሁኔታዎች  የሚቃኘው መጽሐፉ፤ በዋናነትም በዶክተሩ ህልምና ራዕይ፣ በህዝቡ የድጋፍ ምንጮች፣በመደመር እሳቤ፣ በይቅርታና ይቅርታው በወለደው ቅሬታ፣ በመፈንቅለ መንግስት፣ በወቅቱ የአገሪቱ እጣ ፈንታ--- ላይ ሰፊ ትንተና ይሰጣል፡፡
 “… አገራችን ከጦርነት ስጋትና ከገዢዎች በደል ተላቃ የሰላም አየር የተነሰፈችባቸው ጊዜያት ከአንድ ትውልድ ዕድሜ ባይበልጥም፣ ከደርግ ውድቀት በኋላ የተገኘው አንፃራዊ ሰላም ወደፊት ልንደርስበት የምንችለውን የሰላም አየር ከወዲሁ በመገምገም፣ ተስፈኞች ሲያደርገን መቆየቱ ይታወሳል …” በማለት በመጽሐፉ መግቢያ ላይ የገለጹት ደራሲው፤ወደፊት ያሉ ስጋቶችን፣ ተስፋዎችንና የዶ/ር ዐቢይን ፈተናዎች ለመዳሰስ ሞክረዋል፡፡ በ206 ገጾች የተደራጀው መፅሐፉ፤ በ150 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 8761 times