Saturday, 27 October 2018 10:11

የምክር አገልግሎት … በጥራት

Written by 
Rate this item
(2 votes)

 የኢትዮጵያ አዋላጅ ነርሶች ማህበር 27/ኛውን አመታዊ ጉባኤ Oct/12-13/2018/ በአዲስ አበባ አካሄዶአል፡፡ በጉባኤው ላይም በተለያዩ መስተዳድሮች ባሉ የህክምና ተቋማት የሚያገ ለግሉ አዋላጅ ነርሶች እንዲሁም ከተለያዩ የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች የተወከሉ ባለሙያዎች ተሳት ፈዋል፡፡ ጉባኤው በሁለት ቀን ቆይታው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን በተጨማሪም የምርምር ጽሁፎችም ቀርበው ነበር፡፡ ከቀረቡት የምርምር ጽሁፎች ውስጥ አንዱ በቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ላይ ለተጠቃሚዎች የሚሰጠውን የምክር አገልግሎት ጥራትና ብቃት እን ዲሁም መሻሻል የሚገባቸውን ነገሮች የጠቆመው አንዱ ነበር፡፡ ይህን የምርምር ጽሁፍ ያቀረ ቡት ዶ/ር እውነት ገብረሀና ናቸው፡፡ ጥናቱ የያዛቸውን ቁም ነገሮች እንደሚከ ተለው ለንባብ ብለናል፡፡
የቤተሰብ እቅድ ዘዴን የምክር አገልግሎት በሚመለከት በኢትዮጵያ፤ በሜክ ሲኮና በህንድ ጥራቱን የጠበቀ እና ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መረጃን በሚፈ ለገው ደረጃ ለመስጠት እንዲቻል ለማድረግ የተሰራ ጥናት ነው፡፡ ይህንን ጥራቱን የጠበቀ የምክር አገ ልግ ሎት በሚመለከት አገልግሎት በሚሰጥባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ዳሰሳ መደረጉን መረ ጃው ይጠቁማል፡፡
በኢትዮጵያ የጤናው አገልግሎትን በጥራትና በእኩል የማዳረስ ተግባር በጤናው የልማት እቅድ ውስጥ ከተነደፉት እቅዶች ዋነኛው ግብ ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡ የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስ ቴር በነደፈው ብሔራዊ አጀንዳ ውስጥ የጥራት ተግባር አንዱ ሲሆን  ጥራትንም ማሻሻል ሌላው በትኩረት እየተሰራበት ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህም ይህ ጥናት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጥ ራት ማሻሻል ፕሮግራም አስተዋጽኦ ያደርጋል በሚል እንደሚታመን ዶ/ር እውነት ገ/ሐና ገልጸዋል፡፡
ይህ ጥናት በተለይም ሴቶች በቤተሰብ እቅድ ዘዴ አገልግሎት የምክር አሰጣጥ ላይ ምን ልምድ አላቸው? የሚለውን ከተጠቃሚዎች ለማወቅ ሙከራ አድርጎአል። ለዚህም በአዲስ አበባ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ /4/የጤና ጣቢያዎች እንዲሁም /8/ የሚሆኑ የቡድን ውይይቶች /52/የቤ ተሰብ እቅድ ዘዴ ተጠቃሚ ሴቶች እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ ቀደም ሲል ከተደረጉ የዳሰሳ ጥና ቶች የተፈተሸ ሲሆን ውጤቱም እንደሚከተለው ነው፡፡
በጥናቱ እንደተገኘው እውነታ ብዙ ሴቶች አገልግሎቱን የሚሰጡ ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር እና ጥቆማ በቀላሉ የሚቀበሉ ወይንም የሚያምኑ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ የበለጠ እውቀት አላቸው ብለው የሚያምኑት በቀጥታ እነሱ ያገኙዋቸውን የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ሰጪ ዎችን ሆኖ ተገኝቶአል፡፡
አገልግሎት ሰጪዎች ተገልጋዮቻቸውን እንዲያዳምጡ፤ ክብር እንዲሰጡ፤ የተገልጋዮችን የግል ምስጢርን እንዲጠብቁ እና እምነት እንዲጣልባቸው እንዲሁም ከደንበኛቸው የሚነገራቸውን በጥንቃቄ እንዲያደምጡ እና እንዲተገብሩ እንደሚፈለግ ከተገልጋዮች የተገኙ ምስክርነቶች ያረጋግጣሉ። ብዙ ሴቶች እንደተናገሩትም ‹‹…አገልግሎት ሰጪዎች የሚናገሩትን እንድንሰማ ብቻ ሳይሆን እንዲ ያውም ጥያቄ እንድንጠይቅና የምናውቀውን ወይንም የምናምንበትን ነገር እንድንናገር እንዲያበረታቱ ይጠበቅባቸዋል…›› ብለዋል።
ጥናቱ እንደደረሰበት ከሆነ አንዳንድ ሴቶች ካለምርጫቸው ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያውን እንዲወስዱ በአገልግሎት ሰጪዎች ግፊት እንደሚደረግባቸው እና ይህም እምነት እንዲያጡ የሚያ ስችል ድርጊት በመሆኑ ምናልባትም ሴቶች ተመልሰው ወደ አገልግሎት መስጫው እንዳይሄዱ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ይገመታል፡፡
የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ላይ የሚሰጠው የምክር አገልግሎት የተገልጋይዋን የግል መብት እና በራስ የመተማመን ሁኔታዋን የማያበላሽ እና የተከበረ እንዲሆን ተገልጋዮች ይፈልጋሉ፡፡ ደንበኞች የግል መብታቸው ካልተከበረ በተቃራኒው መናገር ወይንም የመናደድ ሁኔታ ሊያሳዩ እና የአገልግሎት መሰኩን ወዳለማክበር ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ ማወቅ ለአገልግሎት ሰጪው ይጠቅማል፡፡
አብዛኞቹ የቤተሰብ እቅድ ዘዴ ተገልጋዮች አገልግሎት ሰጪዎቹ ከተገልጋይ ጋር ሲገናኙ በሚ ኖረው መግባባት ወይንም መነጋገር በሚያስፈልግበት ጊዜ የበለጠ እድል ወይንም ኃይል እንዳ ላቸው ያምናሉ፡፡እንደነዚህ አይነት ሴቶች አገልግሎቱን ለማግኘት በሚኖረው ማንኛውም ድርጊት በትእግስት መጠበቅን ይመርጣሉ፡፡ ለምሳሌም ብዙ ሰአት መጠበቅ ወይንም በአገል ግሎት አሰ ጣጡ ጎደሎ ነገር ቢመለከቱም በትእግስት ሁኔታውን ከመከታተል ውጪ ምንም እርምጃ አይወስዱም ወይንም ጥያቄ አይጠይቁም፡፡
በጥናቱ ከተመለከተው እና ለጥራት አጋዥ ከተባሉት ውስጥ መረጃን የሚመለከት ይገኝበታል፡፡ ከአንዳንድ ተገልጋዮች እንደተገኘው እማኝነት ከሆነ የተለያዩ ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል የሚያስችሉ አገልግሎቶችን ከራሳቸው ምርጫ ውጪ መውሰድ እንደሚችሉ እንደተነገራቸው ይገልጻሉ፡፡ የመከላከያ አይነቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
በክንድ ውስጥ የሚቀበር (NorPlant)
ሉፕ በመባል የሚታወቀው (IUD)
በመርፌ መልክ የሚወሰድ
በኪኒን መልክ የሚወሰድ ነው፡፡
የምክር አገልግሎት ሰጪዎቹ የእያንዳንዱን መከላከያ ዘዴ ጥቅም እና ጉዳት በሚመለከት መረጃ ለተገልጋዮቹ የሚሰጡ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ግን ተገልጋዮቹ ምንም ማብራሪያ ሳይሰ ጣቸው እራሳቸው የመሰላቸውን ወይንም የፈለጉትን ለመውሰድ ወስነው መጠቀም እንደሚ ጀምሩ ተናግረዋል፡፡  
የምክር አገልግሎቱን በሚመለከት ተጠቃሚዎች እንደመሰከሩት የሚነገራቸው ትእዛዛዊ በሆነ መልኩ ይሔንኛው ቢወሰድ ይሻላል በሚል አይነት ሲሆን ለዚህም በክንድ ውስጥ የሚቀበርና ሉፕ የተሰኘውን ዘዴ እንዲመርጡ እንደሚያደርጉዋቸው ይናገራሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መርፌ ውንና በኪኒን መልክ የሚወሰደውን ጤናማ እንዳልሆኑና ብዙ ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን እንደ ሚያስከትል የሚናገሩ የምክር አገልግሎት ሰጪዎች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡
…አንዲት ሴት ከወለደች በሁዋላ በተሰጣት የምክር አገልግሎት ሉፕ የተሰኘውን የመከላከያ ዘዴ ብትወስድ እንደሚሻላት ስለተነገራት እሱዋም እንዲያውም በየጊዜው ወደጤና ተቋሙ እንዳትመላለስ እንደሚረዳት በማመን እንደተቀበለችው ተናግራለች፡፡
በተለያዩ ስፍራዎች ያሉ አማካሪዎች ከሚሰጡት ምክር በመነሳት ሴቶች የአጭር ጊዜ ያልተ ፈለገ እርግዝና መከላከያን ማግኘት እንደማይችሉ አንዳንዴም አቅርቦት እንደማይኖር የመሳሰ ለው ምክንያት ሁሉ ስለሚነገራቸው ብዙዎች ሴቶች ካለምርጫቸው ለረጅም ጊዜ መከላከያ እንደ ተጋለጡ በጥናቱ ግንዛቤ ተወስዶአል፡፡   
አንዲት የ24/አመት እድሜ ያላት ወጣት የሚከተለውን ምስክርነት ሰጥታለች፡፡
‹‹….በመርፌ የሚወሰደውን መከላከያ መውሰድ እፈልጋለሁ ስላቸው እነርሱ ግን እኔ እንድ ወስድ የመረጡት ሉፕ የተሰኘውን ነበር፡፡ እኔ እንደምገምተው …ተገልጋዩ በየጊዜው እየሄደ እንዳያሰለቻቸው የረጅም ጊዜውን ሰጥተው ለመገላገል ያሰቡ ይመስለኛል፡፡እነርሱ የመረጡትን መከላከያ እኔ አላውቀውም፡፡ ወደፊት ምን ጉዳት እንደሚኖረው ምንም ሀሳብ የለኝም፡፡ …›› ነበር ያለችው፡፡
የጥናቱ መደምደሚያ የሚያዘነብለው የተገልጋዮችን ፍላጎት ማስቀደም ይገባል ወደሚለው ነው፡፡ በእርግጥ ብዙ ሴቶች በምክር አገልግሎቱ በተገቢው መንገድ ተገልግለናል ቢሉም በምክር አገል ግሎት አሰጣጡ ምንም አልረካንም ያሉም ቀላል ቁጥር የላቸውም፡፡
ሴቶች ለሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች ተገቢው መልስ አይሰጥም፤
የሚወሰደውን መከላከያ በሚመለከት ስላለው ባህርይ ሙሉ መረጃ አለመስጠት፤
በአማራጭ ሊወሰድ ስለሚችለው የመከላከያ ዘዴ መረጃን አለመስጠት…ወዘተ
ጥናቱ በማጠቃለያው የጠቆመው የቤተሰብ እቅድ ዘዴ የምክር አገልግሎት ሰጪዎች ለተገል ጋዮች ከፍተኛ የሆነ ክብር የሚሰጡ እና እምነት የሚጣልባቸው ከሆኑ ጥራት ላለው የቤተሰብ እቅድ ዘዴ ምክር አገልግሎት አሰጣጥ መሰረት ይሆናል፡፡
የምክር አገልግሎት አሰጣጡ ደንበኞች ስለአገልግቱ ተገቢውን መረጃ እንዲያገኙ በማድረግ እና ባጠቃላይም ተገልጋዩን ያማከለ ቢሆን ጥራት ያለው የምክር አገልግሎት መስጠት ያስችላል… ውጤቱም ይሰምራል ሲል በዶ/ር እውነት ገ/ሐና የቀረበው ጥናት መረጃውን ያጠቃል ላል፡፡

Read 2997 times