Print this page
Saturday, 27 October 2018 10:22

የአዲስ አበባ ንግድ ም/ቤት የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዚዳንት መረጠ

Written by  መንግስቱ አበበ
Rate this item
(2 votes)

በንግድ ዘርፍና በመንግሥት መካከል አገናኝ ድልድይ በመሆን እየሰራ ያለው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፉ ማኅበራት ም/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፕሬዚዳንት መረጠ፡፡
የም/ቤቱ አባላት ከትናንት በስቲያ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባደረጉት 14ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቀድሞ የአባይ ባንክ ፕሬዚደንት የነበሩትን ወ/ሮ መሰንበት ሽንቄጡን የመጀመሪያዋ የአዲስ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት፣ አቶ አበባው መኮንን ም/ፕሬዚዳንትና ሌሎች ዘጠኝ የቦርድ አባላት መርጦ ጉባኤው ተጠናቋል፡፡
በጉባኤው ላይ የምክር ቤቱ የ2010 በጀት ዓመት የሥራ ሪፖርት በቀድሞው ፕሬዚዳንት በአቶ ኤልያስ ገነቲ፣ እንዲሁም የም/ቤቱ ያለፈው ዓመት የሂሳብ መግለጫ በውጭ ኦዲተር ቀር በሪፖርቶቹ ላይ ውይይት ተደርጎ ፀድቋል፡፡
በክብር እንግድነት በጉባኤው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ፣ የከተማችን የንግድ ሥርዓት እንዲሻሻል፣ እንዲሁም የንግዱ ማኅብረሰብና የሸማቹ ኅብረተሰብ ተጠቃሚነት ግምት ውስጥ በማስገባት፣ የሚመለከታቸው የከተማዋ አስተዳደርና የምክር ቤቱ አካላት በማሳተፍ፣ የጋራ ም/ቤት በማቋቋም ወደ ተግባር እንዲገባ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራ መሆኑን ቃል እገባለሁ ብለዋል፡፡
አቶ አብዱልፈታህ ቢሮአቸው፣ ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ህጋዊ እንዲሆኑ እንደሚሰራና እስካሁን ድረስ በህጋዊነት እየሰሩ ባሉት ነጋዴዎች እውቅና ለመስጠት ዛሬ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ የከተማዋ ም/ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ በተገኙበት ሽልማት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
የቀድሞው የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኤልያስ ነገድ ያለፈውን ዓመት የሥራ ክንውን ባቀረቡበት ወቅት የንግዱን ኅብረተሰብ ጥቅም ለማስከበር ተፈላጊ የሆኑ ዘመናዊ አገልግሎቶችን በተሻለ ብቃት ለማቅረብና ተቋማዊ ቁመናውን ለማጠናከር ከአዲስ አበባ መስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ በመገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ አካባ በዝቅተኛ የሊዝ ዋጋ 14 ሚሊዮን ብር 3000 ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቦ ባለ 22 ወለለ የዋና መ/ቤት ሕንፃ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
ም/ቤቱ የንግድና ኢንቨስትመንት ምህዳር እንዲሻሻልና አባላቱ የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች መፍትሄ እንዲያገኙ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አቶ ኤሊያስ በአዲስ አበባ በተለያዩ የንግድ ሥ ላይ የተሰማሩና በተለያየ ደረጃ ያ ግብር ከፋይ አባሎቻችን በግብርና በታክስ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያቀርቡትን ቅሬታ ም/ቤቱ ተቀብሎ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ችግሮች እንዲፈቱ የአድቮኬሲ ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አስረድተዋል ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት፡፡



Read 1752 times