Print this page
Sunday, 28 October 2018 00:00

“ወደ መንገድ ሰዎች” መፅሐፍ ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ገጣሚ መዘክር ግርማን “ወደ መንገድ ሰዎች” የተሰኘ የግጥም መድበል ከነገ በስቲያ ሰኞ ከቀኑ 11፡
00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር እንደሚያስመርቅ ሀዩ ሚዲያና ማስታወቂያ ገለጸ፡፡ አንጋፋዎቹ አርቲስቶች ደበበ እሸቱ፣ ጌትነት እንየው፣ አዜብ ወርቁ እንዲሁም ገጣሚያኑ በረከት
በላይነህ፣ ደሞዝ ጎሽሜ፣ ረድኤት ተረፈ፣ መርዕድ ተስፋዬና ኤልዳ ግዛቸው ከመፅሐፉ ላይ የተመረጡ ግጥሞችን ለታዳሚው ያነባሉ ተብሏል፡፡ የምርቃት ስነ ስርዓቱ “በራዕይ” የኪነት ቡድን በሚቀርብ ሙዚቃና ተውኔት እንደሚታጀብም ታውቋል፡፡ የግጥም መጽሐፉ 58 በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ግጥሞችን ያካተተ ሲሆን በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 4380 times