Print this page
Tuesday, 30 October 2018 00:00

የፋሲል ደሞዝ “ሀገሬ” ኮንሰርት በባህር ዳር ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

ላለፉት አምስት ዓመታት ኑሮውን በአሜሪካ ያደረገው እውቁ የባህል ዘፋኝ ፋሲል ደሞዝ የሚያቀነቅንበት “ሀገሬ” ኮንሰርት ህዳር 1 ቀን 2011 ዓ.ም ምሽት በባህር ዳር ስታዲየም እንደሚካሄድ የኮንሰርቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደስታው ዘመነ ለአዲስ አድማስ ገለፀ፡፡ በበርኖስ ሚዲያና በአስተባባሪ ኮሚቴው ትብብር በሚዘጋጀው ኮንሰርት ላይ ከ60 ሺ በላይ ሰዎች ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለጹት አቶ ደስታው፤በአሁኑ ሰዓት በክልሉ በሚገኙ ከ20 በላይ ከተሞች ላይ ለኮንሰርቱ ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኮንሰርቱ መግቢያ ዋጋ ለመደበኛ 200 ብር፣ ለቪአይፒ 300 ብር መሆኑን የገለጹት አቶ ደስታው፤የኮንሰርቱ አጠቃላይ ዝግጅት 3 ወራትን እንደፈጀም ጠቁመዋል፡፡ ከአድናቂዎቹ ለረዥም ጊዜያት ተለይቶ የቆየው አርቲስቱ፤በኮንሰርቱ ላይ በርካታ ዘፈኖችን እንደሚያቀነቅን የሚጠበቅ ሲሆን ወጣት ድምጻውያንም ሥራቸውን ያቀርባሉ ተብሏል። ፋሲል ደሞዝ ከአገሩ ለመውጣት የተገደደው “ጎንደርን አረሱት” የሚለውን ዘፈኑን ካወጣ በኋላ ሲሆን ጥቅምት 26 አገሩ እንደሚገባም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 4053 times