Saturday, 27 October 2018 10:50

“የጨለማው መጋረጃ ሲቀደድ”ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በደራሲ ሳህሉ አድማሱ የተዘጋጀው “የጨለማው መጋረጃ ሲቀደድ” የተሰኘ መፅሐፍ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ቤሊየር አካባቢ በሚገኘው አዲስ ቪው ኢንተርናሽናል ሆቴል ይመረቃል፡፡ የምረቃ ሥነ ስርዓቱ በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች የሚታጀብ ሲሆን መፅሐፉም ይገመገማል ተብሏል፡፡መፅሐፉ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በሳቸው አመራር የተመዘገቡ ዋና ዋና አስደማሚ ለውጦችን የሰነደ ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩ ያደረጓቸውን ንግግሮችና ያስተላለፏቸውን መልዕክቶችም ያካተተ መሆኑ ታውቋል፡፡ የመፅሐፉም ዋና ዓላማ፤ “ቀጣዩ ትውልድ የመደመርን ሥርዓት፣ የይቅርታንና የፍቅርን ባህል ጠንቅቆ እንዲያውቅና በተግባር ላይ እንዲያውለው፣ኢትዮጵያዊነትን እንዲለማመድ ማድረግ ነው” ይላል - በመጽሐፉ ላይ የሰፈረው ማስታወሻ፡፡ በ108 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ80 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡


Read 2759 times