Monday, 12 November 2018 00:00

“የኢትዮጵያ የተወዛዋዦች የጥበብ ማኅበር” ተመሠረተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮጵያ የተወዛዋዦች የጥበብ ማኅበር ተመስርቶ በይፋ ስራ መጀመሩን የማኅበሩ ሃላፊዎች አስታወቁ። ማኅበሩ ባለፈው ማክሰኞ ረፋድ ላይ በፈንድቃ የባህል ማዕከል በሰጡት መግለጫ፤ የውዝዋዜ ሙያ እንደ ማንኛውም ሙያ የተከበረ ቢሆንም እስከዛሬ ትኩረት ተነፍጐታል፤ ይህንን ሙያና ሙያተኛ ለመጠበቅና ለማክበር  ማኅበሩን መስርተናል ብሏል፡፡
ውዝዋዜ የአንድን ማህበረሰብ ባህል፣ አለባበስ፣ የአኗኗር ዘይቤና የህይወት ፍልስፍና የሚያንፀባርቅና ፕሮዲዩሰር ከዋኝና ፈጠራን የሚጠይቅ በመሆኑ ራሱን ችሎ የሚቆም ሙያ ነው ብለዋል-ኃላፊዎቹ፡፡
ማህበሩ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ አባላትን የሚያቅፍ መሆኑንም የማህበሩ ሊቀመንበሩ የፈንድቃ የባህል ማዕከል ባለቤት፣ ተወዛዋዥ አቶ መላኩ በላይ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ ማህበሩ ወደፊትም በሮያሊቲ ክፍያ አሰባሰብ፣ በባለሙያው መብትና ሙያውን ከፍ በማድረግ ዙሪያ ጠንክሮ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡


Read 3229 times