Monday, 12 November 2018 00:00

“የፅህፈት ፋና” በገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ውብ፣ ቀላልና ጊዜ ቆጣቢ የአማርኛ ቃላት አፃፃፍ ማስተማሪያ መጽሔት በገበያ ላይ ዋለ፡፡ የ“የፅሕፈት ፋና” በማንኛውም ዕድሜና የእውቀት ደረጃ ለሚገኙ ሁሉ የሚጠቅም የአፃፃፍ ክህሎት የሚያዳብሩ ይዘቶችንና መልመጃዎችን ማካተቱ ታውቋል፡፡
የማስተማሪያ መጽሔቱ አዘጋጅ ለረጅም ጊዜ ያካበቱትን እውቀት ያፈሰሱበትና በዘርፉ ስመጥር  ምሁራን ከሽፋን ስዕሉ ጀምሮ በየገፆቹ ያሉት ደጋፊ ስዕሎች፤ የእውቁ ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ሥራዎች እንደሆኑ በመፅሐፉ የመጀመሪያ ክፍል ተገልጿል፡፡ “የፅህፈት ፋና” በምርምር በመስክ ምልከታና በተግባራዊ ሙከራ ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ ሲሆን የተማሪዎችና የመንግስት ሰራተኞች የእጅ ፅሕፈቶች በናሙናነት ተወስደው የጥናቱ አካል እንደሆኑም ታውቋል፡፡ በ67 ገፆች የተቀነበበው ማስተማሪያ መጽሔቱ በ100 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 3380 times