Monday, 12 November 2018 00:00

“መፅሐፍት የህይወት ቅመም ናቸው” አውደ ርዕይ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 ሰምና ወርቅ ኢንተርቴይንመንት የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ “መፅሐፍት የህይወት ቅመም ናቸው” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የመፅሐፍት አውደ ርዕይ ከትላንት በስቲያ በመገናኛ አደባባይ ተከፈተ፡፡
ከቦሌ ክ/ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር በትብብር በተዘጋጀው የመፅሀፍት አውደ ርዕይ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ተባባሪ ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ የተገኙ ሲሆን፤  አንጋፋ ደራሲያንና መጽሐፍት አድናቂዎችም ታድመውበታል፡፡
ከ20 እስከ 50 በመቶ የዋጋ ቅናሽ የተደረገባቸውና አዳዲስ የጠፉ መፅሐፍት ለገበያ የሚቀርቡበት ይህ አውደ ርዕይ፤ የፊታችን ረቡዕ ድረስ እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል፡፡  

Read 6309 times