Print this page
Saturday, 10 November 2018 12:47

የቀድሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ጦር ሰራዊት ማኅበር ተቋቋመ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(10 votes)

 “መንግሥት ይጠቀምብን፤ ሃገራችንን ማገልገል እንፈልጋለን”

     የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት አባላት፤ ሃገር አቀፍ ማኅበር መመስረቱን አስታወቁ፡፡
ባለፈው እሁድ በርካታ የቀድሞ የጦር ሰራዊት አባላትና አመራሮች በአዲስ አበባ ተሰብስበው ስለማኅበሩ ምስረታ ምክክር አድርገዋል ተብሏል።
በዚህ ማኅበር የቀድሞ ምድር ጦር፣ አየር ኃይልና ባህር ኃይል አባላት መካተታቸውን የጠቆሙት የማኅበሩ ምስረታ አስተባባሪ መቶ አለቃ ሰለሞን አደመ፤ በቀጣይ ማኅበሩ አድማሱን በማስፋት በየቦታው በተለያየ ሁኔታ ላይ የሚገኙ የጦሩን አባላት ያሰባስባል ብለዋል፡፡
ማኅበሩ በዋናነት የሰራዊቱ አባላት የጋር ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁበት፣ እርስ በእርስ የሚረዳዱበት እንዲሁም መንግስት ሙያዊ እገዛቸውን በፈለገ ወቅት ለሃገራቸው የሚያገለግሉበት እንደሚሆን መቶ አለቃ ሰለሞን ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡
በማኅበሩ ምስረታ ላይ ተጋብዘው የተገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አዛዥ ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ በበኩላቸው፤ መንግስት የቀድሞ ሰራዊት አባላትን እውቀትና አቅም ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል፡፡

Read 9147 times