Saturday, 19 May 2012 11:10

አሌክ ባልድዊን ተፈላጊ ሆኗል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

የ54 ዓመቱ አሌክ ባልድዊን በተለያዩ የፊልም ስራዎች ተፈላጊ በመሆን ትኩረት መሳቡን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ “ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር” እንዳስታወቀው፤ አሌክ ባልድዊን ከእንግሊዛዊው ኮሜድያን ራስል ብራንድ ጋር “ማን ዛት ሮክስ ዘ ክራድል” በተባለ የኮሜዲ ፊልም ስራ ላይ እየተሳተፈ ሲሆን ሁለቱ ተዋናዮች ከቶም ክሩዝ ጋር በሰሩትና በብሮድዌይ በሚታየው “ሮክ ኦፍ ኤጅስ” የተባለ ሙዚቃዊ ቲያትር ድንቅ ቅንጅት አሳይተዋል፡፡ በዲያሬክተር ውዲ አለን በሚሰራው “ቱ ሮም ዊዝ ላቭ” በተባለውና በአሁኑ ግዜ ቀረፃው በኒውዮርክና ሳን ፍራንሲስኮ በሚከናወንለት ሌላ ኮሜዲ ፊልም ላይም አሌክ ባልድዊን በመሪ ተዋናይነት እንደሚሳተፍ ታውቋል፡፡

በታዋቂው የቴሌቭዥን ተከታታይ የኮሜዲ ፊልም “30” ሮክ ላይ በአስቂኝ ትወናው የገነነው አሌክ ባልድዊን፤ ከ30 ዓመታት በላይ በቆየበት የትወና ሙያው በመላው ዓለም 4.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱን የጠቆመው የቦክስኦፊስ ባይነምበርስ መረጃ፤ አንጋፋው ተዋናይ በሚሰራው አንድ ፊልም በአማካይ እስከ 44 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያስገኝ አመልክቷል፡፡አሌክ ባልድዊን ከቲም ሞርጋንና ከቲና ፌይ ጋር የሚሰራው “30 ሮክ” ከሰባት ዓመታት በኋላ ዘንድሮ መገባደዱ የተገለጸ ሲሆን አሌክ ባልድዊን በኤንቢሲ ቻናል በሚተላለፉ የኮሜዲ ትርኢቶች ላይ መስራት እንደበቃው ተናግሯል፡፡

 

 

Read 2801 times Last modified on Saturday, 19 May 2012 11:16