Saturday, 24 November 2018 13:00

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ዲፓርትመንቱን ወደ ት/ቤት ሊያሳድግ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


ከሁለት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ የዓለም የቴአትር ማኅበር (ITA) አባል እንድትሆን አቅም የፈጠረው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ዲፓርትመንት ወደ ት/ቤት ሊያድግ መሆኑ ተገለፀ፡፡ ከትናንት በስቲያ ረፋድ ላይ የዩኒቨርሲቲው የቴአትር ዲፓርትመንት ኃላፊዎች በብሔራዊ ቴአትር ከባለድርሻ አካላትና ከአንጋፋ የቴአትር ባለሙያዎች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ምክክር ያደረጉ ሲሆን ከምክክሩም ዲፓርትመንቱን ወደ ት/ቤት ለማሳደግ የሚጠቅሙትን ግብአቶች ማግኘቱን የቴአትር ዲፓርትመንት ኃላፊው አቶ አስተዋይ መለሰና አቶ ወርቁ ገልፀዋል፡፡ አቶ አስተዋይ ጨምረው እንደተናገሩት፤ ዲፓርትመንቱ እንደ ዳይሬክቲንግ፣ ፕሌይ ራይቲንግ፣ አክቲንግ፣ ፕሮዳክሽን ዲዛይን፣ ቴክኖሎጂ፣ አርት ማኔጅመንትና ፊልም ያሉት ትልልቅ ዲሲፕሊኖች ያሉት ቢሆንም በዲፓርትመንት ብቻ ተሸጉጦ አስፈላጊውን ትምህርትም ሆነ ውጤት ለተማሪዎች መስጠት ባለመቻሉ ወደ ት/ቤት እንዲያድግ አስፈላጊውን ምክረ  - ሀሳብ (ፕሮፖዛል) አሰናድተው ለባለ ድርሻ አካላት በማቅረብ፣ አስፈላጊ ግብአት መሰብሰባቸውን ተናግረዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱን ጨምሮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከብሔራዊ ቴአትር የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ዲፓርትመንቱ ወደ ት/ቤት እንዲያድግ ይጠቅማል ያሉትን ሀሳቦችና ምክሮች አጋርተዋል፡፡


Read 856 times