በቢዝነስና ኪነ ጥበብ ዘርፎች ሥልጠናዎችን እየሰጠ የሚገኘው “ልቀት ቢዝነስ እና አርት ኮሌጅ” ሁኔታዎች ሳይመቻቹላቸውና መክፈል ሳይችሉ ቀርቶ ወደ ኪነ ጥበብ ሙያ ለገቡ አርቲስቶች ነፃ የትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው፡፡ ኮሌጁ ከጊዜ ወደ ጊዜ ራሱን በማሳደግና አቅሙን በመገንባት፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ የማደግ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ ሲሆን ብዙ የቢዝነስና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን እያፈራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የኪነ ጥበቡን ዘርፍ ለማሳደግና ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት መክፈል የማይችሉ አርቲስቶችን በነፃ ተቀብሎ ለማስተማር መዘጋጀቱን የኮሌጁ የትምህርት አስተዳደር ኃላፊ ዲን አስታውቀዋል፡፡ የነፃ ትምህርት ዕድሉ መጠቀም የሚፈልጉ ከህዳር 17 እስከ 30/2011 ዓ.ም ባሉት ቀናት አራት ኪሎ ትምህርት ሚኒስቴር ጀርባ በሚገኘው አይሲቲማርት ህንፃ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው የኮሌጁ ቢሮ መመዝገብ እንደሚችሉም ኃላፊው ገልፀዋል፡፡
Saturday, 24 November 2018 13:06
“ለአርቲስቶች ነፃ የትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና