Saturday, 24 November 2018 13:08

“የፖለቲካ አሽሙር” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)


በአንጋፋው ጋዜጠኛና በ2006 ዓ.ም በጋዜጠኝነትና የሚዲያ ዘርፍ የበጎ ሰው ተሸላሚ በሆኑት አጥናፍ ሰገድ ይልማ የተፃፈው “የፖለቲካ አሽሙር” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል፡፡
መጽሐፉ ወቅታዊውን የአገሪቱን የፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች በአሽሙር የሚያቀርብ ነው ተብሏል፡፡ አንጋፋ ጋዜጠኛና የጋዜጠኝነት መምህር ማዕረጉ በዛብህ በጀርባው ገፅ ላይ በሰጡት አስተያየት፤ “በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ፣ እስከዛሬ ያልተሞከረና የሚያስደንቅ የፖለቲካ አሽሙር” ሲሉ ገልፀውታል፡፡ በ95 ገፆች የተዘጋጀው መጽሐፉ በ60 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 6512 times