Saturday, 19 May 2012 11:27

“ጣጠኛው” እና “አውቶሞቲቭ” መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃሉ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈው የአንጋፋው ደራሲ፣ ተርጓሚና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ 54ኛ ሥራ የሆነው “ጣጠኛው” የተሰኘው መፅሃፍ ዛሬ ይመረቃል፡፡ ከቀኑ 8፡30 አትላስ ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ዮሊ ሆቴል መጽሐፉ ሲመረቅ የደራሲው ባለቤት ወይዘሮ አልማዝ ገብሩ በክብር እንግድነት እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በዝግጅቱም የደራሲውና የሌሎች ፀሐፍት የግጥም ሥራዎች ለታዳሚዎች ይቀርባሉ፡፡

በሌላ በኩል የማርክና ሃብትሽ አጠቃላይ አውቶሞቲቭ ሥራዎች ቴክኒካል ማኔጀርና የ”አውቶሞቲቭ ጆርናል” የሬዲዮ ዝግጅት አማካሪ የሆኑት አቶ ሃብታሙ ኃይሌ ያዘጋጁት” አውቶሞቲቭ ጆርናል” መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል፡፡ በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት ትንሿ አዳራሽ ከጧቱ 3 ሰዓት የሚመረቀው መጽሐፍ አሽከርካሪዎችን፣ መካኒኮችን፣ የቴክኒክ ተማሪዎችን፣ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን፣ እግረኞችን እና አዲስ መንጃ ፍቃድ አውጪዎችን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ መጽሐፉ በ35 ብር ይሸጣል፡፡

 

 

Read 2070 times Last modified on Saturday, 19 May 2012 11:29