Print this page
Saturday, 15 December 2018 14:55

“በትግራይ እስካሁን የፖለቲካ እስረኞች አልተፈቱም” አረና

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 አለመፈታታቸውን የገለፀው አረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉአላዊነት (አረና)፣ የዲሞክራሲ ምህዳሩ እንዲሰፋ ጠይቋል፡፡
በትግራይ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች እስካሁን ሁለት የአረና አመራር አባላትን ጨምሮ መሠረቱን ኤርትራ አድርጐ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረው የትህዴን ሰባት አባላት አሁንም በትግራይ እስር ቤቶች በእስር ላይ እንደሚገኙ ፓርቲው ለአዲስ አድማስ አስታውቋል፡፡  ዶ/ር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸውን ተከትሎ፣ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች የተፈቱ ቢሆንም በትግራይ ግን እስካሁን በእስር ላይ እንደሚገኙ አረና አስታውቋል፡፡
የአረና እና የትህዴን የፖለቲካ እስረኞች ከእስር አለመለቀቃቸውን የተናገሩት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አምዶም ገ/ስላሴ፤ ከክልሉ መንግስት ጋር በጉዳዩ ላይ መነጋገራቸውንና በደብዳቤ መፃፋቸውን ጠቁመው እስካሁን ግን ምላሽ አላገኘንም ብለዋል፡፡ የክልሉ መንግስት በሌላው የሀገሪቱ ክፍል እንደተደረገው ሁሉ በትግራይም የፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈታ፣ ዲሞክራሲውንም እንዲያሠፋ አረና ጠይቋል፡፡
አረና የትግራይን ህዝብ መብት በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ጽኑ አቋም እንዳለው የጠቆመው ድርጅት፤ ህወሓትንና ፖሊሲውን አምርሮ እንደሚታገልም አስታውቋል፡፡   

Read 1021 times