Saturday, 15 December 2018 14:59

በቀን ከ8 ሰዓታት በላይ መተኛት ለልብ ህመም የመጋለጥ እድልን ይጨምራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የካናዳና የቻይና ተመራማሪዎች በጋራ የሰሩትን ጥናት መሰረት በማድረግ ከሰሞኑ ይፋ ያደረጉት መረጃ፣ በቀን ከ8 ሰዓታት በላይ የሚተኙ ሰዎች ለልብና ለደም ቧንቧ ህመሞች የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል፡፡
የካናዳው ኤምሲማስተር ዩኒቨርሲቲና የቻይናው ቢጄንግ ፉዋይ ሆስፒታል ተመራማሪዎች ከ21 የአለማችን አገራት በተውጣጡ 117 ሺህ ያህል ሰዎች ላይ ላለፉት 8 ተከታታይ አመታት ባከናወኑት ሰፊ ጥናት፣ በቀን ከ6 እስከ 8 ሰዓታት ብቻ የሚተኙ ሰዎች በበሽታ የመጠቃትና የሞሞት እድላቸው ዝቅ ያለ መሆኑን እንዳረጋገጡ አስታውቀዋል፡፡
ለረጅም ሰዓታት መተኛትም፣ ለአጭር ሰዓታት መተኛትም ለልብና ለሌሎች በሽታዎች የማጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ቢሆንም፣ ለአጭር ሰዓታት ከመተኛት ይልቅ ለረጅም ሰዓታት መተኛት የበለጠ ለበሽታ አጋላጭ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል ተመራማሪዎቹ፡፡
በቀን ከ8 እስከ 9 ሰዓታት መተኛት ለልብና ለደም ቧንቧ ህመሞች የመጋለጥ እድልን በ5 በመቶ ከፍ ያደርጋል ያሉት ተመራማሪዎቹ፣ እስከ 10 ሰዓታት መተኛት በ17 በመቶ፣ ከ10 ሰዓታት በላይ መተኛት ደግሞ እስከ 41 በመቶ ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

Read 1348 times