Saturday, 15 December 2018 15:01

የአለማችን አየር መንገዶች 885 ቢ. ዶላር ገቢ እንደሚያገኙ ተገምቷል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በመጪው የፈረንጆች አመት 2019 በአለማችን የሚገኙ አየር መንገዶች በድምሩ 885 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅና ይህም በታሪክ ከፍተኛው ገቢ እንደሚሆን አለማቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር አያታ ማስታወቁን ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል፡፡
አለማቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር አያታ ያወጣውን መረጃ ተቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ በመጪው አመት የተሸለ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ይኖራል ተብሎ ከመገመቱ ጋር በተያያዘ የአለማችን አየር መንገዶች አጠቃላይ ትርፍ ከአምናው በ10 በመቶ ያህል ጭማሪ በማሳየት 35.5 ቢሊዮን ዶላር ያህል ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አለማችን አየር መንገዶች በመጪው የፈረንጆች አመት የሚያጓጉዟቸው መንገደኞች ቁጥር አምና ከነበረው በ5.6 በመቶ በማደግ 4.6 ቢሊዮን ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ማህበሩ መግለጹንም ዘገባው አመልክቷል፡፡ በ2018 በበርሜል 73 ዶላር የሚሸጠው የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በመጪው አመት ወደ 65 ዶላር ዝቅ ይላል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቆመው ዘገባው፣ የአለማችን አየር መንገዶች በአመቱ ለነዳጅ ብቻ 200 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አክሎ ገልጧል፡፡

Read 1293 times