ለእኛ ግን ዛሬም ውድነህ
ዛሬም ደማቅ ነህ፡፡
በክብር ከልባችን ትኖራለህ
ቤተሰቦችህ
(አሰፋ ጎሳዬ የአዲስ አድማስ መሥራችና ባለቤት ነበር)
አትጠራጠር አሴ
ዛሬም አለህ ነገም አለህ!
ሁሌ ስለምናስታውስ
አለህ እኛጋ በመንፈስ ውስጣችን
አለህ ዳር ድረስ!
አገርህም ዛሬም አለች
እየተንገዳገደች
አንድ ምዕራፍ ዘላለች
ስለዚህም
አብረኸን ነህ
ዛሬም አለህ
ነገም አለህ!!
Published in
ጥበብ