Saturday, 05 January 2019 10:42

የግል ንጽህናን በመጠበቅ ጤንነትን መጠበቅ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

ጉርምስና ወይንም ኮረዳነት ከልጅነት የእድሜ ክልል በመውጣት በአካልም ይሁን በአስተሳሰብ እንዲሁም በማበራዊ ጉዳዮች ለውጥ የሚታይበት እድሜ ነው፡፡ ይታያሉ ከሚባሉት ለውጦች መካከልም ሴቶች በኮረዳነት ወይንም በልጃገረድነት እድሜያቸው የሚያዩት የወር አበባ አንዱ ነው፡፡
የወር አበባ በትክክለኛው መንገድ ጤናን ለመጠበቅ የሚያስችል የጽዳት ድርጊት እንዲፈጸም የሚያስፈልግበት ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው፡፡ ልጃገረዶች ወይንም ሴቶች የወር አበባ በሚመጣ ጊዜ ችላ በማለት ጤንነትን መጠበቅ የሚያስችል የንጽህና ዘዴን ካልተጠቀሙ በሰውነታቸው ላይ ኢንፌክሽን እንዲከሰት ምክንያት ሊፈጠር እንደሚችል ባለሙያዎች ያረጋግጣሉ፡፡ ዶ/ር ሙሉቀን አዛገ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጥናት እንደገለጹት ልጃገረዶች እንዲሁም ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ጊዜ ፍሳሹን ለመቆጣጠር የሚጠቀሙባቸውን ፓዶች እንዲሁም የሚለብ ሱዋቸውን  የውስጥ ሱሪዎች እና የገላቸውን ጽዳት የፓዱንም ሆነ የውስጥ ሱሪውን  የአለዋ ወጥ ስርአት በመጠበቅና በማጽዳት በኩል ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ለአስተሳሰባቸውም ይሁን ለአካላቸው ጤንነት በጣም ይጠቅማል፡፡ የግል ጤናን መጠበቅ በተለይም ለወር አበባ መቀበያነት የሚጠቀሙበትን እና ለጠቅላላው ጥንቃቄ የሚውለውን የውስጥ ሱሪ በምን ያህል ጊዜ ማስወገድ እንደሚገባ አስቀድሞ ማሰብ እና መተግበር ለሕምም ከመጋለጥ ያስወግዳል፡፡  
ሴቶች በትምህርት ወይም በባህል እና ማህበራዊ ኑሮ ስርአት ወይንም ከገንዘብ አቅም ማነስ ጋር በተያያዘ በሚኖር ቸልተኝነት የተነሳ በሽንት መሽኛ አካባቢ የሚከሰት መጥፎ ጠረን ያለው ሽታ ወይንም ኢንፌክሽን ሲያጋጥማቸው ይታያል። በተለያዩ ባላደጉ ሀገራት ያሉ ልጃገረዶች ስለወር አበባ ሁኔታ እና በምን መንገድ ማስተናገድ እንደሚጠበቅባቸው የሚያገኙት መረጃ ውስን ነው፡፡ ወላጆች ወይንም ትምህርት ቤቶች ይህንን በግልጽ ለልጃገረዶቹ መረጃ እንዳይሰጡ ከሚያደርጉዋቸው መካከልም ስለወር አበባ ከልጆች ጋር ማውራት እንደነውር ወይንም አሳፋሪ ተደርጎ የሚቆጠርበት በልማድ ይዘው የቆዩት አጋጣሚ በመኖሩ ነው፡፡
በኮረዳነት እድሜ ላይ ሆነው የወር አበባን ማየት የጀመሩ ልጃገረዶች ተፈጥሮን የሚጋፈጡት ምንም አውቀት እና ዝግጁነት ሳይኖራቸው መሆኑን በማደግ ላይ ያሉ የተለያዩ ሀገራት መረጃ ዎች ያሳያሉ፡፡ ልጃገረዶቹ ከዚህም የተነሳ ግራ የመጋባት፤ ፍርሀት እና ሀፍረት ስለሚሰማ ቸው የዚህም መጨረሻ ጭንቀት እና የወር አበባ በሚያዩ ጊዜ እራሳቸውን ከማህበራዊ ግንኙ ነት ማራቅን ይመርጣሉ፡፡ ከወላጆቻቸው የሚያገኙት ድጋፍ ደካማ የሆነ እንዲሁም ከአስተማ ሪዎች ምንም ድጋፍ የማይደረግላቸው እና የወር አበባ መቀበያን መግዛት አለመቻል፤ በትምህ ርት ቤታቸው ጽዳታቸውን ለመጠበቅ በቂ ውሀና መጸዳጃ ስፍራው ጭምር ምቹ ያለመሆን ለል ጃገረዶቹ ትልቅ ችግር ይሆናሉ፡፡ በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ ጥናቶች እንደታየው ከሆነ በገጠር እና በከተማ ያለው ሁኔታ ልዩነት በመጠኑ ሆኖ ይታያል ይታያል፡፡
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባዎች የተለያዩ ማህበራዊና ባህላዊ እንዲሁም በግልጽ ውይይት ማድረ ግን በሚመለከት የተለያዩ ልምዶች በመኖራቸው ከወር አበባ ጋር በተያያዘ ለሚኖረው የጤንነት አጠባበቅ በጎ ያልሆነ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ እሙን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወጣቶችን ያማከለ የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት በየጤና ተቋማቱ ቢኖሩ ልጃገረዶቹ የራስን የስነተዋልዶ ጤና በመጠበቁ ረገድ ማወቅ የሚገባቸወን እንዲያውቁ ያስችላል፡፡ በዚህ ላይ በመመስረት በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉ ጥናቶች የወር አበባ እና የጤና አጠባበቅን በሚመለከት ምን ጠንካራ እና ደካማ ጎን አለ የሚለውን ለይቶ ለማወቅ እና የስነተዋልዶ ጤናን በሚመለከት ያለውን እውነታ ለመረዳት ያስችላል፡፡  ይህ ጥናትም መሰረት ያደረገው እውነታ ከላይ የተገለ ጸውን ሲሆን የተመለከተውም  በአገሪቱ ሰሜን ምእራብ አቅጣጫ በባህርዳር የገጠር እና ከተ ሞች አካባቢ ከወር አበባ ጋር በተያያዘ ያለውን የጤና አጠባበቅ ሁኔታ ነው፡፡
ጥናቱ የተደረገው በውጭው አቆጣጠር Feb/2015 ሲሆን ጥናቱ በተደረገበት ወቅት እና በተደረ ገበት አካባቢ የነበሩ ልጃገረዶች ሁሉም እንዲካተቱ ተደርገዋል፡፡ የከተማ ልጃገረዶች 50% እንዲሁም የገጠር ልጃገረዶች 40% እና ሌሎች 10% የተካተቱበት ሲሆን በድምሩ 1010/ አንድሺህ አስር ልጃገረዶች በጥናቱ ተካተዋል፡፡ የተገኘው ውጤት የሚያሳየው የሚከተለውን ነው፡፡
የወር አበባን ተከትሎ የሚተገበረውን የጽዳት ተግባር በተመለከተ የተለያዩ ሁኔታዎች አፈጻጸሙ ላይ በጎ ወይንም ጎጂ ተጽእኖ እንደሚያደርሱ በጥናቱ ታይቶአል፡፡ እነርሱም
(…እድሜ፤ የወር አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየበት እድሜ፤ የጋብቻ ሁኔታ፤ ትምህርት…) ናቸው፡፡ ሌላው በጥናቱ ትኩረት የተደረገበት የወር አበባ መቀበያን ፓድ አጠቃቀም፤ የተጠቀሙበትን ፓድ የማስወገድ ሁኔታ፤ በቀን ምን ያህል ጊዜ ገላቸውን እንደሚታጠቡ የሚያሳዩ መልሶችን የሚጋብዙ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡
ልጃገረዶች ወይንም ሴቶች የሚሰጡት መልስ፡-
ንጹህ የወር አበባ መቀበያ ፓድ እንደሚጠቀሙ፤
የተጠቀሙበትንም ሲያስወግዱ በተገቢው መንገድ ማለትም ሽንት ቤት ውስጥ መጣል በመሳሰለው መንገድ መሆኑ፤
ብልትን ጨምሮ በአካባቢው ያለውን ገላቸውን በቀን ሁለት ጊዜ ወይንም ከዚያ በላይ የሚታጠቡ ከሆነ፤
ከወር አበባ ጋር በተያያዘ የግል ጤናን የመጠበቁ ሁኔታ ብቁ ነው ያሰኛል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ለኢንፌክሽን የመጋለጥ ነገር ሊከተል ስለሚችል ብቁ አይሆንም፡፡ በዚህ መመዘኛ መሰረት በተደ ረገው ጥናት የተገኘው ውጤት የሚያሳየው ከከተማ 29.5% ከገጠር ደግሞ 21.9% የሚሆኑት ልጃገረዶች በወር አበባቸው ጊዜ ንጽህናቸውን ጠብቀዋል የሚያስችል ተግባር እየፈጸሙ መሆ ኑን ነው፡፡
ልጃገረዶች ወይንም ሴቶች በወር አበባ ጊዜ ንጽህናቸውን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ወይንም የማያስችሉአቸው ነገሮች የተለያዩ ናቸው፡፡
የወር አበባ መቀበያ ፓድ የመሳሰሉት አቅርቦት እንደልብ የማይገኝባቸው መኖሪያ አካባቢዎች፤ የልጃገረዶቹ የትምህርት ሁኔታ፤ የእናቶች አለመማር፤ የልጃገረዶቹ በትምህርት ላይ መሆን፤ የጋብቻ ሁኔታ፤ የወር አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመጣበት እድሜ፤…ወዘተ
የመሳሰሉት ነገሮች ልጆቹ ጤንታቸውን በጠበቀ መንገድ ተፈጥሮን እንዲያስተናግዱ የሚያደርጋቸው ግንዛቤ እንዲኖራቸው ግድ የሚልበት ሁኔታ ነው፡፡   
በተደረገው ጥናት የታየው ውጤት የገጠርና የከተማ ልጃገረዶች ዘንድ ብዙም ልዩነት አይታይም፡፡ በሁለቱም ዘንድ በግዢ የሚገኘውን የወር አበባ መቀበያ የሚጠቀሙም፤ የማይጠ ቀሙም የጥናት ተሳታፊዎች ታይተዋል፡፡ ፈሳሽን ለመቀበል የሚያስችሉ ፓድ ሳይሆን ጨርቆ ችን የሚጠቀሙ ልጃገረዶች ቁጥርም (75.3%) ቀላል ሆኖ አልተገኘም፡፡ የተጠቀሙበትን በትክ ክለኛው መንገድ በማስወገድ ረገድ አብዛኞቹ የገጠር ልጃገረዶች የሚጠቀሙበት መንገድ ተቀባ ይነት ያለው ሆኖ ተገኝቶአል፡፡ ምናልባትም በከተሞች አካባቢ ጥቅም ላይ የሚውሉ መታጠቢያ ቤቶች የወር አበባ ፓድ ለመጣል አስቸጋሪ ሆነው ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡
ልጃገረዶች በወር አበባ ጊዜ  ከትምህርት እንደሚቀሩ የተለያዩ አገራት ጥናቶች ጭምር ያሳያሉ፡፡ይህም በቁጥር ሲሰላ ከከተማ ልጃገረዶች 1/4ኛ/ከገጠር ደግሞ 1/5ኛ የሚሆኑ ናቸው፡፡ የዚህም ምክንያቱ የተለያየ ሲሆን ነገር ግን በቂ የሆነ የወር አበባ መቀበያ አለመኖር ወይንም ጽዳትን ለመጠበቅ የሚያስችል ዝግጅት እንዲሁም ወደትምህርት ቤት ሊሄዱ የሚችሉት ረዥም መንገድ ተጉዘው ሊሆን ስለሚችል እና ሌሎች ተመሳሳይ ችግሮችን ማስተናገድ ስለሚከ ብዳቸው …ወዘተ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡  
ጥናቱ በማጠቃለያው እንደገለጸው ከሆነ ሴቶች የወር አበባን የሚያስተናግዱት ጤንነ ታቸውን ለመጠበቅ በሚያስችል ሁኔታ ነው ለማለት የሚያስደፍር አይደለም፡፡ ጥናቱ በተደረ ገባቸው አካባቢዎች የተገኘው ውጤት ዝቅተኛ ሲሆን ወደ 24.5% ነው፡፡ በጥናቱ መረጃ  መሰረት በገጠርና በከተማ በሚኖሩ ልጃገረዶች መካከል ያን ያህል የሚባል ልዩነት አልተገኘም፡፡ ቢሆንም ግን በከተሞች አካባቢ ያሉ ልጃገረዶች የወር አበባ መቀበያን መጠቀማቸው ከገጠሩ ይልቅ ከፍ ያለ ነው፡፡ በእድሜ ከፍ ማለት፤ በመደበኛው ትምህርት መካፈል ወይንም የልጃ ገረዶቹ እናቶች ትምህርት ሁኔታ ትክክለኛውን ጤንትን ለማግኘት የሚረዳ የጽዳት ሁኔታን ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚያግዝ በጥናቱ ተደርሶበታል፡፡ ስለዚህም ኮረዳዎች ወይንም ልጃገ ረዶች የወር አበባን ተፈጥሮአዊ ሁኔታ አውቀው እና በምን መልክ ጽዳትን በጠበቀ መልኩ ማስተ ናገድ እንደሚጠበቅባቸው ከቤተሰብ እንዲሁም ከትምህርት ቤት ወይንም ከሌሎች ማለ ትም ታዳጊዎችን ባማከለ መንገድ መዘጋጀት ከሚገባቸው መድረኮች መረጃ መገኘት አለበት፡፡ ልጃገረዶቹ ተፈጥሮአዊ ሁኔታው ከመከ ሰቱ በፊት ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማስቻል ያስፈልጋል ዶ/ር ሙሉቀን አዛገ በጥናቱ እንደገለጹት፡፡

Read 2487 times