Print this page
Sunday, 06 January 2019 00:00

“የፕላስቲክ ውዳቂን ወደ ጥቅም መቀየር--” መፅሐፍ ወጣ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በፀሐፊና አዘጋጅ ሲሳይ ክፍሌ የተሰናዳው “የፕላስቲክ ውዳቂን ወደ ጥቅም በመቀየር የአካባቢ ብክለትን መቀነስ (የፕላስቲክ ውዳቂ አያያዝ መመሪያ)” መፅሐፍ በሳምንቱ መጀመሪያ  መውጣቱ ተገለጸ፡፡
መፅሐፉ ዓለም አቀፍ ችግር የሆነውንና ለብዙ መቶ ዓመታት የማይበሰብሰውን ፕላስቲክ እንዴት መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚቻል ተግባራዊ ትምህርት ይሰጣል ተብሏል፡፡
አዘጋጁ በመግቢያው ላይ ባሰፈረው መልዕክት፤”መፅሐፉ የተዘጋጀው ትኩረቱን የአካባቢ ብክለት ላይ ብቻ አድርጎ አይደለም፡፡ ቆሻሻዎችም ሆነ የፕላስቲክ ውዳቂዎች በውስጣቸው ገንዘብና ዕድገት እንዳለ ለማሳየት ጭምር መሆኑን አንባቢውም ሆነ የመጽሐፉ ተጠቃሚ ግንዛቤ እንዲኖረው ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡” ብሏል፡፡ በ70 ገጾች የተሰናዳው መፅሐፉ፤ በነፃ የሚታደል መሆኑም ታውቋል፡፡

Read 2166 times