Sunday, 06 January 2019 00:00

“ተቤራ እና ሌሎችም” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በወጣቱ ደራሲና ኮምፒዩተር ኢንጂነር ሚካኤል አስጨናቂ የተጻፉ ከ20 በላይ ወጎችን አካትቶ የያዘው “ተቤራ እና ሌሎችም” የተሰኘ የወግ መድበል ለንባብ በቃ፡፡
ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በኮምፒዩተር ምህንድስና በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቆ፣ በኮምፒዩተር ምህንድስናና በኔትወርክ ኢንጂነሪንግ ሙያ እየሰራ የሚገኘው ወጣቱ፤ ”የነፍስ ጥሪው የሆነውን ስነ ፅሁፍ እውን ለማድረግ” የወግ ስብስቦች ፅፎ ማሳተሙን በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ጠቁሟል፡፡
በ315 ገጾች የተመጠነው መፅሐፉ፤በ91 ብር ከ50 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡
ወጣቱ ደራሲ፤ በማህበራዊ ሚዲያ በሚፅፋቸው ወጎችና ግጥሞች የሚታወቅ ሲሆን በሁለተኛው “ጣና ሶሻል ሚዲያ አዋርድ” በስነ-ፅሁፍ ዘርፍ እጩ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

Read 1550 times