Saturday, 12 January 2019 14:49

የአፄ ቴዎድሮስ 200ኛ ዓመት ልደት ሰኞ ይከበራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 የሚሊኒየሙ ጀግና እየተባሉ የሚወደሱት አፄ ቴዎድሮስ 200ኛ ዓመት የልደት በዓል የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር አዘጋጆቹ “የእምዬ ምኒልክ ወዳጆች ማህበር” አስታውቋል፡፡
በክብረ በዓሉ ግጥሞች፣ የታሪክ ትንተና፣ የበገና ዝማሬ፣ ፉከራና መነባንብ የሚቀርብ ሲሆን፤ ረዳት ፕ/ር አበባው አያሌው፣ የሙዚቃ ሃያሲው ሰርፀፍሬ ስብሃት፣ ገጣሚ ይታገሱ ጌትነት፣ ዶ/ር ዘሪሁን ሙላቱና ሌሎችም ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡

Read 7804 times