Print this page
Saturday, 12 January 2019 14:49

በአንዳንድ “የፊቶች ፊት” የግጥም መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 የጋዜጠኛና ገጣሚ ሰለሞን ኃይለየሱስ ግጥሞችን ያካተተው በአንዳንድ “የፊቶች ፊት” የተሰኘ የግጥም መድበል በገበያ ላይ ዋለ፡፡
በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በየእለት ህይወታችን ላይ የሚያተኩሩ ከአርባ በላይ ግጥሞችን ያካተተው መጽሐፉ፤ የኋላ ማንነታችንን ከዛሬ ህይወታችን ጋር እያያያዘ፣ ስነ ምግባርን በተቃርኖ የተሞላ የሰውን ልጅ ባህርይን እንዲሁም በርካታ ጥልቅ ጉዳዮችን ይዳስሳል፡፡ በ63 ገጽ የተመጠነው መጽሐፉ፤ በ60 ብር ከ70ሣ. ለገበያ ቀርቧል፡፡ ገጣሚው ከዚህ ቀደም “የልብ ዓይን” የተሰኘ የግጥም ሲዲ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

Read 7565 times